የካናዳ ኢምባሲ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርትን ለማጎልበት በጋራ ለመስራት መስማማቱ ተገለጸ

0
543

አዲስ አበባ የሚገኘው የካናዳ ኢምባሲ በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምሀርት ተቋማትን ለማጠናከርና ድጋፍ ለማድረግ ከኢፌዲሪ ሳይነስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለማስራት ስምምነት ላይ መድረሱን አስታወቀ። ኢምባሲው በቴክኒክና ሙያ፣ በሳይነስና በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ድጋፍ ለማድረግና ለማጠናከር የተስማማ ሲሆን ሴቶችን በማብቃት እንዲሁም በሌሎች የጋራ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መደረሱንም ለማወቅ ተችሏል። የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ አፈወርቅ ካሱ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የካናዳ አምባሳደር አንቶይን ቼቭሪየር ትናንት ጥር 6/2012 ተገናኝተው በተወያዩበት ወቅት በካናዳ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን አገራቸውን በተለይም ደግሞ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውስጥ የተጀመረውን ለውጥ የሚደግፉበትንም መንገድ መክረዋል። ከዚሁም በተጨማሪም ካናዳ ለኢትዮጵያ በምትሰጠው የውች የትምህርት ዕድልም ሰፊ ውይይት አድርገዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here