ረቡዕ ህዳር 25ቀን2017 (አዲስ ማለዳ)ባለፈው ዓመት 28 ባንኮች በድምሩ 1ነጥብ3 ቢሊዮን ብር እንደተጭበረበሩ ተገልጿል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ አመታዊ የፋይናንሺያል ደህንነት ሪፖርቱንይፋ ባደረገበት ወቅት ባንኮቹ እንደተጭበረበሩ የገለጸ ሲሆን ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ3መቶ ሚሊዮን ብር ብልጫ አለው ተብሏል።
በሪፖርቱ መሰረት በሀገሪቱ ከሚገኙ ሰላሳ አንድ ባንኮች ውስጥ 28ቱ የተጭበረበሩ እና ሀሰተኛ ምንዛሪ መጠቀምን ጨምሮ የተሰረቁ የኤቲኤም ማሽኖች፣ የውሸት ቼኮች፣ የተጭበረበሩ የስልክ መልዕክቶች እና ሌሎች ተዛማጅ መንገዶች እንደሚገኙ ተመላክቷል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባንኮች ብድር ለመስጠት ከአነስተኛ ብድርና ቁጠባ ተቋማት ጋር የሚያደርጉት ትብብር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ከበይነመረብ ማጭበርበር ጋር ተያይዞ እየጨመረ ለመጣው የገንዘብ ኪሳራ አስተዋፅዖ እንደሚያደርግ ተገልጿል።



