ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን 50ኛ ዓመት ሊያከብሩ ነው

0
633
ኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን የጀመሩበትን የ50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል ለማክበር በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ጥር 8 ቀን 2012 በሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ። አገራቱ 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዩቤልዩ በዓል በሚያከብሩበት ጊዜ የ50 ዓመት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸዉን የጉዞ ዳራ መቃኘት፣ በኹለቱ አገራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ የመጣዉን የኹለትዮሽ ግንኙነት በኹለቱ አገራት ሕዝቦችና በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ግንዛቤ እንዲፈጠር ለማድረግ እንደሚሠራ ተገልጿል። የኹለቱን አገራት የወደፊት ግንኙነት ይበልጥ በማጠናከር፣ በኹለትዮሽ እና በባለ ብዙ መድረክ ግንኙነት ያላቸዉን ትብብር በአፍሪካ እንዲሁም በምሥራቅ አፍሪካ ያላቸውን የትብብር ደረጃ ከፍ ማድረግ እና ኹለቱ አገራት በፋይናንስና ቴክኒክ ትብብር፣ በእዉቀትና ቴክኖሎጅ ሽግግር ማንፀባረቅና ትብብሩ የሚጠናከርበትን እድል መፍጠር መሆናቸዉ በመግለጫዉ ተመላክቷል። የኢትዮጵያ እና ቻይና ዲፕሎማሲያዊ ትስስር በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ1970 ጀምሮ 50 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በተለይ ከ 2017 ጀምሮ ግንኙነታቸዉ ወደ ሁሉን ዐቀፍ ስትራቴጃዊ ትብብር ማደጉን ተከትሎ፣ በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ወታደራዊ በሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ ለማጠናከር  መቻሉን ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አስታውቋል። እንዲሁም የኹለቱ አገራት ግንኙነት መንግሥት ከመንግሥትና ፓርቲ ከፓርቲ እንዲሁም ተቋም ከተቋም እንዲሆን እድል መፍጠሩ ተገልጿል። ቅጽ 2 ቁጥር 63 ጥር 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here