ባለፉት ስድስት ዓመታት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን የሚያቋርጡ ተማሪዎች ቁጥር ሰባት በመቶ ጨመረ

0
660

ከ2007 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲጨምር የቆየው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የማቋረጥ መጠን በ 2011 በሰባት ነጥብ በመቶ በማሻቀብ 17.5 በመቶ ሆኖተመዘገበ።

ከ 100 የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ውስጥ በ2005 16ቱ ትምህርታቸውን ያቋርጡ የነበረ ሲሆን፣ ይህም በ2006 ከፍተኛ መቀነስ በማሳየት ከመቶው ተማሪዎች ውስጥ ስምንቱ ብቻ ትምህርታቸውን አቋርጠው እንደነበር የብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ ሪፖርት ያሳያል። ነገር ግን በ 2007 ተመልሶ የጨመረው የማቋረጥ መጠን መሠረት ከመቶ ተማሪዎች ዐስሩ አቋርጠዋል።

በተከታታይ ለሦስት ዓመታት መጠነኛ ጭማሪ ብቻ በማሳየት ቆሞ የነበረው የመቋረጥ መጠን በ 2011 ግን በ2010 ትምህርታቸውን ካቋረጡ ተማሪዎች በሰባት ተማሪዎች ከፍ በማለት በመላው አገሪቱ ካሉ የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ውስጥ 17.5 በመቶ የሚሆኑት ትምህርታቸውን ማቋረጣቸውን የብሔራዊ ባንክ የትምህርት ዘርፍ ሪፖርት አመላክቷል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ዮሃንስ ዎጋሶ ለአዲስ ማለዳ ሲያብራሩ፣ ችግሩ ከዚህም ቀደም በተለያዩ ምክንያቶች እንደነበር አስታውሰዋል። ትምህርት ሚኒስቴር የለመዱት ምክንያት ብለው በጠቀሱት የትምህርት ቤቶች በየአካበቢው ላይ በአማራጭ አለመበራከት፣ የትራንስፖርት ችግር እና ኅብረተሰቡ የኢኮኖሚ ሁኔታ በአንድም ሆነ በሌላ አጋጣሚ ተማሪዎቹን የትምህርት ገበታቸው ላይ እንዳይገኙ ከሚያስተጓጉላቸው የተለመዱ

ምክንያቶች ላይ እየተሠራ እንደሆነ ገልጸው፣ ነገር ግን ከ 2010 አስከ 2011 ያለው የትምህርት ዘመን በተለይም በክልል አካባቢ ካሉ ተማሪዎች ጋር በተያያዘ የመጡትን ከአገሪቷ አለመረጋጋት ጋር አያይዘው የመጠነ ማቋረጡ ቁጥር እንዲያሻቅብ እድሉን ከፍ አድርጎታል ብለዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በዚህ ሳቢያ ሊያስከተል የሚችለውን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ አንስተው፣ መንግሥት እንደመፍትሄ እየሠራባቸው ነው ያሏቸውን ጉዳዮችም ጠቅሰዋል። በ2011 ከፍተኛ የመጠነ ማቋረጥ እንዲከሰት ካደረጉ ምክንያቶች መካከል የተፈጠረው አለመረጋጋት አንዱ ነው ብለዋል። ‹‹መንግሥት የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ነበሩበት በሚመለሱበት ጊዜ በአፋጣኝ ወደ ትምህርት

ገበታቸው እንዲመለሱ ሁኔታዎችን ማመቻቸት ላይ ነው›› ሲሉ ኃላፊው ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። ‹‹ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እስኪመለሱም ባሉበት አካባቢም ሆነው ትምህርታቸውን መቀጠል እንዲችሉ በአቅራቢያቸው ባሉ ትምህርት ቤቶች እንዲመዘገቡ የማድረግ አሰራር ዘርገተናል።›› ሲሉም አክለዋል። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል ኃላፊ የዓለም ሎሬት ጥሩሰው ተፈራ (ፕሮፌሰር) እንደገለፁት፣ የጉዳዩ ተፅእኖ እና የሚያመጣው ጉዳት በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።

‹‹ከሚያመጣው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ተጽእኖ አንጻር መንግሥት በአፋጣኝ የትምህርት ተቋማትን በፖለቲካ ሰዎች

ሳይሆን በባለሙያዎች እና ለቦታው የሚመጥን የትምህርት ደረጃ ባላቸው ሰዎች መመራት እና መተዳደር ይገባዋል›› ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል። ፕሮፌሰሩ አክለውም፣ ለአብዛኛው ግጭት እና ለመጠነ ማቋረጥ መጨመር ምክንያት የሆነውን ግጭት ከመሰረቱ መፍታት ያስፈልጋል ብለዋል። በተለይም ብሔርን መሰረት ያደረጉ ጉዳዮች ሳቢያ ጥቃት የሚደርስባቸውን ተማሪዎች ትኩረት አድርጎ ጥበቃ ካልተሰጠ፣ ተማሪዎች ደኅንነታቸውን ለመጠበቅ ሲሉ ከትምህርት ገበታ ይቀራሉ ሲሉም ያብራራሉ።

ቅጽ 2 ቁጥር 63 ጥር 9 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here