የወመዘክር አዳራሽ ከኹለት ሳምንት በኋላ ተጠናቆ ለአገልገሎት ክፍት ይሆናል

0
996

በ1.3 ሚሊዎን ብር በእድሳት ላይ የቆየዉ ወመዘክር አደራሽ ከሁለት ሰምንት ብኋላ ተጠናቆ ለአገልገሎት ክፍት እንደሚሆን ተገለፀ። የእድሳት ስራው ከአሜሪካን ኤምባሲ በተገኘ 1ነጥብ 3 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ በነሀሴ ወር ተጀምሮ እስከ ጥቅምት ወር እንደመሚጠናቀቅ ሲጠበቅ የነበረ ቢሆንም በአጋጠሙ የዲዛይን ችግሮች ስራው ሊጓተት ችሏል።

አዳራሹ 120 ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለዉ ሲሆን በዋናነት የድምፅ እና የመብራት ችግሮችን ተስተካክልዉ በአዳራሹ ዉስጥ ጥናታዊ ጽሑፎችን በምስል በማቅረብ፡ ፊልሞችን ማሳየት እንድችል እና የመጸዳጃ ቤትን ጨምሮ መሰል ገልግሎቶችን መስጠት በሚስቸውል ምልኩ እድሳቱ እንደተከናወ ነግረዉናል። በቀጣይ ኹለት ሳምንታት ውስጥም ስራውን በማጠናቀቅ በአዳራሹ መፅሐፍትን ለሚያስመርቁ ሰዎች ቀጠሮ እንደሰጡ የኤጀንሲዉ ስራ አስኪያጅ ይኩኖአምላክ መዝገቡ(ደ/ር) ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

እድሳቱ በአሁኑ ጊዜ ለመጠናቀቅ ሌሎች ስራዎችን አጠናቆ የቀለምና የመብራት ስራዎች እንደቀሩትና ይኩኖአምላክ (ዶ/ር) ለአዲስ ማለዳ ገልፀዉ እድሳቱ የዘገየበት ምክንያት እድሳቱን የሚደረገዉ ኮንትራክተር አማካሪ ስለሌለዉ የአሰራር ስተት ተፈጥሮ የተሰሩ ስራዎች ዳግም እንድሰሩ መደረጋቸዉ መሆኑን የኤጀንሲዉ ስራ አስኪያጅ ለአድስ ማለዳ ተናግረዋል።

ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተመጽሀፍት ኤጀንሲ ‹‹ የሕዝብ ቤተመጽሐፍት ወመዘክር›› በሚል ስያሜ በ1936 ዓ.ም በቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ተመርቆ የተከፈተ ሲሆን አገልግሎት መስጠት የጀመረዉም ንጉሱ ባነረከቱት ከ 200 በላይ የመጻሕፍት ስጦታ ነብር። ኤጀንሲዉ በአሁኑ ስዓት የ24 ስዓት የቤተ መጽሐፍት አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን በተጨማሪም ኢትዮጽያዉያን ደራሲያንና ጸሐፍያን ለመጸሐፍ ስራቸዉ አዉቅና የሚገኙበትና በዓለም አቀፍ ደረጋ በድረ ገጽ ገብያ መጽሐፍቶቻቸዉን ለመሸጥ የሚያሰችላቸዉን የመጽሐፍ መለያ ቁጥር ይሰጣል።

ቅጽ 2 ቁጥር 64 ጥር 16 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here