ዳሰሳ ዘ ማለዳ (ጥር 20/2012)

0
838

 

የትግራይ ክልል በቅርቡ ከአዲስ አበባ እና ከፌደራል መንግሥት ከሥልጣናቸው ለተነሱ የሕወሓት ባለሥልጣናት ሹመት ሰጠ። በዚህም መሠረት የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር የነበሩት ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሔር በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የፍትሕ ዘርፍ አስተባባሪ ሲሆኑ፤ በምክተትል ከንቲባ ማዕረግ የምጣኔ ሀብት ዘርፍ አስተባባሪና የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ሰለሞን ኪዳኔ (ዶ/ር) በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የትግራይ ከተሞች ክትትል ኃላፊ ተደርገው ተሾሙ። የሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባልና የመንግሥት ተጠሪ ሚንስትር የነበሩት አስመላሽ ወልደሥላሴ የክልሉ የበይነ መንግሥታት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነዋል።(አሃዱ ቴሌቪዥን)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

በኦሮሚያ ክልል የምስራቅ ሃረርጌ ዞን ባሉ የተለያዩ ከተሞች ወደ አዲሰ አበባ የሚወስዱ መንገዶች በዛሬው ዕለት ተዘግተው መዋላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲሰ ማለዳ ተናገሩ። ሀሮማያ፣ አወዳይ እና ሐረር ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች መንገዶች፣ የትምህርት ተቋማት፣ የንግድ ቦታዎች፣ ባንኮች እና አገልግሎት ሰጪ ተቋማት መዘጋታቸውንም ጨምረው ገልፀዋል። ከመንገድ መዘጋቱ በሻገርም በሐረር ከተማ የጎማ ማቃጠል ጭምር እንደታየ የከማው ነዋሪ ተናግረው አመሻሹ ላይ ግን የመከላከያ ሰራዊት ወደ ከተማው ገብቶ ማረጋጋት መጀመሩን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። መንገዶች የተዘጉበት ምክንያትም በወለጋ የተለያዩ ዞኖች  የቴሌኮሚኒኬሽን መቋረጥ እና ሎሎች ተግባሮች እንዳስቆጧቸው በመግፅ እንደነበር እንዲሁም ተቃውሞው እስከ አርብ ድረስ እንደሚቀጥል በሰፊው መረጃው እንዳለም የሐረር ከተማ ነዋሪ ተናግረዋል። (አዲሰ ማለዳ)

 

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

 

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ ) የኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ መጠባበቂያ ገንዘብ  በቀጣዩ ስድስት ወራት  ውስጥ ወደ 4 ቢሊየን ዶላር ሊደርስ እንደሚችል ተነበየ። በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ የወውጪ ምንዛሬ መጠባበቂያ ሁለት ነጥብ ስምንት ቢሊዮን  ዶላር  ሲሆን መጠባበቂያ ገንዘቡ ወደ አራት ቢሊዮን ሊደርስ እንደሚችል ይጠበቃል ብሏል። ለዚህም በምንያትነት የሀገር ውስጥ የገንዘብ ፍሰት መሻሻል እደሚኖር  እና ኢትያዮጰያ ከአንድ ወር በፊት ከአይ ኤም ኤፍ  ያገኘቸው ሶስት ቢሊዮን ዶላር የገንዘብ ብድር ማፅቁ የውጭ ምንዛሬ መጠባቢቂያ ክምችቱን ሊያሳድገው ይችላል ተብሏል።(ኢትዮጵያን ቢዝነስ ሪቪው)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

በሕገ-ወጥ መንገድ ዓለም አቀፍ ጥሪ በማስተላለፍ ኢትዮ ቴሌኮምን ከአምስት ሚሊዮን ብር በላይ እንዲያጣ ያደረገው ተከሳሽ በዘጠኝ ዓመት ጽኑ እስራትና በገንዘብ መቀጮ ተቀጣ። ተከሳሹ ያለፈቃድ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ወደ ሀገር ዉስጥ በማስገባት፣ በመጠቀም እና የቴሌኮም አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ሳይኖረው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ከግለሰብ ቤት በመከራየት ሲሠራ መቆየቱ ተገልጿል። የኢትዮ ቴሌኮም ሲም ካርዶችን በውስጣቸው በማስገባት በአንድ ጊዜ ብዛት ያላቸው ጥሪዎችን በቅናሽ ማስተላለፍ ከመጋቢት 30 ቀን 2010 እስከ ጷጉሜ 01 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ መስራቱ ተመላክቷል።(የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

በምስራቅ አፍሪካ አገራት የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል 70 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግ ኦክስፋም አስታወቀ። በተለይም በኢትዮጵያ፤ ኬኒያ እና ሶማሊያ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ለመከላከል ገንዘቡ ሚሊዮን ዶላር የሚስፈልግ ሲሆን አገራቱ በፍጥነት ለጉዳዩ መፍትሄ ካልሰጡት የአንበጣ መንጋው እስከመጪው ሰኔ ወር ድረስ ከነበረበት በአምስት መቶ እጥፍ እንደሚበዛ ኦክስፋም ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ኡጋንዳና ደቡብ ሱዳንም የአንበጣ መንጋው በቀጣይ በከፍተኛ ሁኔታ የሚከሰትባቸው አገራት ናቸው ተብሏል። በኢትዮጵያ የአንበጣ መንጋው ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ በአማራና ትግራይ ክልል በመቶ ሺህ ስኩዌር ኪሎሜትሮች በሚገመት ስፍራ ላይ ያሉ እጽዋቶችን አውድሟል። (ኢዜአ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

 

በሶማሌ ክልል ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በትናንትናው ዕለት በቁጥጥር ስር ዋሉ። የሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ከጅግጅጋ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኘው መጋሎቀረን መቆጣጠሪያ ጣቢያ ባደረገው ድንገተኛ ፍተሻ  ነው በቶጎጫሌ ድንበር በህገወጥ መንገድ በአንድ ተሽከርካሪ ተደብቆ ሊገባ የነበረ 39 ሽጉጥ ከተጠርጣሪዎቹ ጋር መያዙ የጠቆመው። የክልሉን ልዩ ኃይል ህገ ወጥ መሳሪያውን ይዘው የነበሩት ሶስት ተጠርጣሪዎች እና አንድ ተሽከርካሪ ተይዟል።(ፋና)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………..

ኮካ ኮላ የለስላሳ መጠጦች በኢትዮጵያ ለሚያደርገው የማስፋፊያ ፕሮጀክት ከስታንዳርድ ባንክ የ50 ሚሊዮን ዶላር ወይም አንድ ነጥብ ሰድስት ቢሊዮን ብር ብድር ማግኘጡን አስታወቀ።ብድሩ የተሰጠው ለድርጅቱ የአፍሪካ ቅርጫፍ ኮካ ኮላ ቤቬሬጅ አፍሪካ ሲሆን ገንዘቡም የሚውለው በኢትዮጵያ የኮካ ኮላ አምራች የሆነው ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ ለሚያደርገው ማስፋፊያ ነው። ድርጅቱ ብድሩ መሰጠቱን የስታንዳርድ ባንክ የግንኙነት ሃላፊ ሲሞን ሪቭስ ቢዝነስ ሪፖርት ለተባለው የደቡብ አፍሪካ ሚዲያ አረጋግጠዋል።
ኢስት አፍሪካ ቦትሊንግ እያስገነባ ባለው አዲሱ ፋብሪካው ላይ እስካሁን ሁለት ነጥብ አንድ ቢሊዮን ብር (70 ሚሊዮን ዶላር) ወጪ ያወጣ ሲሆን ግንባታው ሲጠናቀቅ የማምረት አቅሙን 70 ሺህ ካሳ(ሳጥን) ያሳድጋል። (አዲስ ማለዳ)

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here