ኢህአዴግ እንዲፈርስ ምርጫ ቦርድ በሙሉ ድምጽ ወሰነ

0
803

 

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) በሊቀመንበሩ በኩል በፃፈው ደብዳቤ ግንባሩ መፍረሱን ለቦርዱ ያሳወቀ ሲሆን አስፈላጊውን ማጣራት በማድረግ በሙሉ ድምፅ ኢህአዴግ አንዲፈርስ ወሰነ።

እንዲሁም ህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ (ሕወሃት) በሊቀመንበሩ በኩል በጻፈው ደብዳቤ ግንባሩ በመፍረሱ የንብረት ክፍፍልን አስመልክቶ ቦርዱ ውሳኔ እንዲሰጥበት በጠየቀው መሰረት በብልጽግና እና በህወሃት መካከል የኢህአዴግን ንብረት ክፍፍል ማድረግ እንደሚገባም በተመሳሳይ ቦርዱ ውሳኔ አሳልፏል።

በዚህ መሰረትም ብልጽግና እና ህወሃት የኢህአዴግ ንብረትና ሂሳብ የሚያጣራ አጣሪ በጋራ ሰይመው በኢህአዴግ ስም ያለ ማናቸውም እዳ ተጣርቶ እንዲከፈል ቦርዱ አዟል። ከእዳ ክፍያ ቀሪ የሆነ ሃብት 3/4ተኛው ለብልጽግና ፓርቲ ( የሶስቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ውህደት በመሆኑ) ¼ተኛ ደግሞ ለህወሃት ድርሻ መሆኑ ታውቆ በዚያ መሰረት ክፍፍል እንዲያጠናቅቁም አሳስቧል።

እነዚህን ትእዛዞች ፓርቲዎቹ ፈፅመው በህጉ መሰረት በ6 ወር ውስጥ ለቦርዱ እንዲያሳውቁ አዞ ውሳኔውም በፅሁፍ እንደሚደርሳቸው ገልጿል።

አዲስ ማለዳ ሁለቱ ፓርቲዎች ጥያቄአቸውን ለቦርዱ ባቀረቡበት ወቅት የሰራችውን ዘገባ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ይመልከቱ (https://addismaleda.com/archives/9331)

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here