ዳሰሳ ዘ ማለዳ (የካቲት 10/2012)

0
574

 

በጉራፋርዳ ወረዳ ከተከሰተው ሁከት ጋር በተያያዘ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ክልል ጉራፋርዳ ወረዳ በትናንትናው ዕለት የካቲት 09/2012  ከተከሰተው ሁከት እና ብጥብጥ ጋር በተያያዘ የወረዳው አስተዳዳሪን ጨምሮ የተለያዩ የስራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከልም  ኩንዲሳ ንጉሴ የወረዳው አስተዳዳሪ፣ ሃይሉ ይግለጡ የወረዳው ድርጅት ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣ ቢሰጥ ወርቁ የአቃቤ ህግ ጽህፈት ቤት ሃላፊ፣ኦይሳ አለሙ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ፣ ታጋይ ሳሙኤል ኮጃ የማዘጋጃ ቤት ሃላፊ እና ሌሎች ባለሙያዎች ይገኙበታል ተብሏል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ኤዜማን ጨምሮ  ለስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ እና የሕጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጠ።ከተሰጣው መካከል ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ መላው አማራ ህዝብ ፓርቲ፣ ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ)፣ አፋር ነጻ አውጪ ግንባር ፓርቲ ( አነግፓ) እና የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ይገኙበታል፡፡ (ማለዳ ምርጫ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በአካባቢው በተፈጠረ አለመረጋጋት የተነሳ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ የዩኒቨርስቲው ሴኔት ካደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በኋላ መወሰኑን ታውቋል፡፡ተማሪዎቹም ለሦስት ተከታታይ ሳምንታት ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወስኗል። ከባለፈው ሳምንት ጀምሮ ከአስተዳደራዊ የመዋቅር ጥያቄ ጋር ተያያዘ በሸካ ዞን ሚዛን ቴፒ ከተማ ግጭት ተቀስቅሶ የሠው ህይወት ሲጠፋ ንብረትም መውደሙ ተገልጿል። (ቢቢስ አማርኛ)

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ኢትዮጵያ እያካሄደች የሚገኘውን ለውጥ ለመደገፍ አሜሪካ ከፍተኛ ማዋዕለ ነዋይ እንደምታፈስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ማይክ ፖምፒዮ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ከአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዮ ጋር ተወያይተዋል፡፡  ኢትዮጵያ በማህበራዊ ፣ ፓለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ዘርፎች እያካሄደች የሚገኘውን ማሻሻያ አሜሪካ እንደምትደግፍ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መናራቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ሃላፊ ንጉሱ ጥላሁን ውይይቱን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቀዋል፡፡(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በአምስት ኪሎ ሜትር ርቀት ውስጥ ምስል መለየት የሚያስችል የደህንነት ካሜራ በአዲስ አበባ አገልግሎት ላይ ለማዋል እንቅስቃሴ መጀመሩን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በዘርፉ ልምድ ካለው ድርጅት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ቴክኖሎጂውን መዘርጋት በሚችሉበት ሁኔታ ላይ የመከሩ ሲሆን የሚገጠሙት የደህንነት ካሜራዎች ወንጀልን ቀድሞ በመከላከል ዜጎች ደህንነት ተሰምቷቸው እንዲኖሩ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡ (የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት የኮሮና ቫይረስ ምልክቶች ታይተውበት በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኝ አንድም ሰው እንደሌለ የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ከቻይና ውጭ ያሉ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እየገቡ ከሚገኙ መንገደኞች በተጨማሪ ችግሩ ከታየባቸው 25 አገራት የሚመጡ መንገደኞች ላይም ጥብቅ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን አስታውቋል፡፡የሙቀት ልየታው ብቻውን ማስተማመኛ ባለመሆኑ በአየር መንገዱ የሚገቡ መንገደኞች ከገቡ በኋላ በሚኖሩት ቀናት በባለሙያዎች ተጨማሪ ክትትሎች እንደሚደረግባቸውም አስታውቋል፡፡(ኢቢሲ)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ባለፉት 6 ወራት የኦሮሞን ህዝብ ፍላጎትና ጥቅምን ያስከበሩ ስራዎች ተከናውነዋል ሲሉ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ የካቲት 10/2012  የጨፌ ኦሮሚያ አምስተኛ የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ባቀረቡት የክልሉ መንግሥት የስድስት ወር የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ  ተናገሩ፡፡የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሞን ሕዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ለማስከበር እና ለማረጋገጥ፣ ክልሉ ውስጥ ሰላም እና መረጋጋትን ለመፍጠር እንዲሁም ወደ ብልፅግና የሚደረገው ጉዞ እንዲሳካ እየሠራ ነው ሲሉም ጠቁመዋል፡፡ (የኦሮሚያ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት)

……………………………………………………………………………………………………………………………………………………………… በአማራ ክልል በቱሪስት መዳረሻ ስፍራዎች የመሰረተ ልማት አለመሟላት የጎብኚዎች ቁጥርና በዘርፉ የሚገኘው የገቢ መጠን በሚፈለገው ልክ አለመሆኑን የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ። የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መላኩ አላምረው እንደተናገሩት የክልልን ኢኮኖሚ በከፍተኛ መጠን መደገፍ የሚችሉ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ የቱሪስት መስህብ ስፍራዎች በብዛት ይገኛሉ ።የመስህብ ሃብቶችን የሚጎበኙ የሃገር ውስጥም ሆነ የውጭ ሃገራት ቱሪስቶች ቁጥር እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም በዘርፉ ካለው ሃብት ብዛት ልክና በሚፈለገው ደረጃ እያደገ አለመሆኑን ተናግረዋል። በችግሩ ምክንያት በግማሽ ዓመቱ ከ8 ሚሊዮን በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ቱሪስቶች ክልሉን ይጎበኛሉ ተብሎ ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አካባቢውን የጎበኙ ቱሪስቶች ቁጥር ግን 7 ሚሊዮን መሆኑም ተጠቆመዋል፡፡(ኢዜአ)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here