በአማራ ክልል ከ720 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም ተያዘ

0
768

በአማራ ክልል ከ720 ሺሕ ሄክታር በላይ መሬት በአደገኛና መጤ አረም መያዙን የአማራ ክልል የእፅዋት ዘርና ሌሎች ግብርና ግብዓቶች ጥራት፣ ቁጥጥር እና ለይቶ ማቆያ አስታወቀ።
የክልሉ የእፅዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብዓቶች ቁጥጥር እና ለይቶ ማቆያ ባለሥልጣንና የሜዳ ፕሮጀክት ትብብር፥ በአደገኛና መጤ አረም መከላከልና ፀረ ተባይ ኬሚካል ጥራት ቁጥጥር አያያዝና አጠቃቀም ዙሪያ ውይይት የተደረገ ሲሆን፣ በክልሉ እንቦጭ አረምን ጨምሮ 12 አደገኛና መጤ አረም መኖሩን የፀረ ተባይ ኬሚካል፣ ማዳበሪያና ቁጥጥር ባለሙያ ሞገስ ዘውዱ ባቀረቡት ሪፖርት ገልጸዋል።

በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች 720 ሺሕ 424 ሄክታር መሬት በአደገኛና መጤ አረም መያዙን ሞገስ ጠቅሰዋል።
አደገኛና መጤ አረም በአገር አቀፍ ደረጃ 30 በመቶ ምርትና ምርታማነትን የሚቀንስ እና በጤና እንዲሁም በነባር የአገር ውስጥ ዝርያ ተክሎች ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ለአደገኛና መጤ አረም በክልሉ መንግሥት የተሰጠው ትኩረት ማነስ፣ ባለድርሻ አካላት የመከላከል ሥራውን ለግብርና ቢሮ ብቻ መተዋቸው እና የቅንጅት ሥራ አለመኖር አረሙ እንዲስፋፋ ማድረጉ በውይይቱ ላይ ተነስቷል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ከ2007 ጀምሮ አደገኛና መጤ አረም የመከላከልና የመቆጣጠር ሥራ ቢሠራም፣ የቅንጅት እና የትኩረት ማነስ ችግሮች በመኖራቸው የተፈለገውን ውጤት ማምጣት እንዳልተቻለ አስታውቋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 68 የካቲት 14 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here