ምርጫ ቦርድ ኢዜማ እየተገለገለበት ያለውን ጽኀፈት ቤቶች ለኢዴፓ እንዲመልስ ጠየቀ

0
852

 

 

የኢትየጵያ ምርጫ ቦርድ በአሁን ወቅት የኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) እየተገለገለባቸው የሚገኙትን ሦስት ጽኀፈት ቤቶች እንዲመልስ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ስለመጠየቁ የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ)  ለአዲስ ማለዳ ገለጸ።

ምርጫ ቦርድ የሦስቱ ጽኀፈት ቤቶች ባለቤትነት የኢዴፓ መሆኑን ጠቀሶ፣ ለፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በየካቲት 17/2012 በጻፈው ደብዳቤ ላይ ከኢዜማ በማስመለስ ለፓርቲያችን እንዲያስረክብ ተጠይቋል ሲሉ የኢዴፓ ፕሬዝዳንት አዳነ ታደሰ ገልጸዋል።

አዳነ፣ ምርጫ ቦርድ አስቀድሞ ይህን ነገር መፍታት ሲኖርበት ዘግይቶም ቢሆን ተገቢ እርምጃ መውሰዱን በመልግለፅ ቀጣዩ ስራችን የቤቶች ኮርፖሬሽን አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወስድ መጠየቅ ነው ብለዋል።

ኢዴፓ በኢዜማ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ጽኅፈት ቤቶቹ መመለሳቸውን እርግጠኛ ሲሆን ክሱን  ሊያቋርጠው እንደሚችል ጠቁሟል።

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here