ዮሃንስ ቧያለው የመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ሹመታቸውን አልቀበልም አሉ

0
916

የቀድሞው የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዮሃንስ ቧያለው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በመለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ዋና ዳይሬክተርነት እንዲያገለግሉ የሰጧቸውን ሹመት እደማይቀበሉ አስታወቁ።

ዮሃንስ ለአማራ መገናኛ ብዙሃን በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ በፌደራል ደረጃ ምደባ እንደሚሰጣቸው እንጂ የትኛው መስሪያ ቤት አንደሚመደቡ እውቅናው እንዳልነበራቸው ተናግረዋል።

ሹመታቸውንም በዜና መስማታቸውን አክለው ለዚህም ተቋሙ አሁን በህዝብ ዘንድ ያለው አመለካከት በተቋሙ መስራት እንደማያስችላቸው እና ይህንንም ሪፖርት ማድረጋቸውን ለአማራ ብዙሃን መገናኛ ገልፀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here