በጎንደር ከተማ 13 ካናዳውያን ታሰሩ

0
928

ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በጎንደር ከተማ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ 13 ካናዳውያን በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

በከተማው ባሳለፍነው ዓርብ የካቲት 20/2012 አንድ የካናዳ ግብረ ሠናይ ድርጅት  13 ሠራተኞቹ ጊዜው ያለፈበትን መድሐኒት ሲያሰራጩ እንደነበር ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ዘጋርድን ዘግቧል።

ተጠርጠረው ከታሰሩት መካለም ኹለት ኢትዮጵያውን ሰራተኞች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።

የካናዳው ግብረ ሠናይ ድርጅት በበኩሉ  ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት ባለሙያዎች የተማሩ እና ብቃት ያላቸው መሆኑን በመግለፅ በካናዳ ሲሰጡት ከነበረው የሕክምና አገልገሎት የተለየ አልሰጡም ሲል በድኅረ ገጹ ላይ አስታውቋል።

በጉዳዩ ላይም የካናዳ እና የኢትዮጵያ መንግስት ይነጋገራሉ ተብሎም ይጠበቃል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here