ዳሰሳ ዘ ማለዳ (የካቲት 24/2012)

0
366

በአማራ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች በዳኞች ላይ የሚፈጸም ጥቃት እየተበራከተ መምጣቱ ተገለጸ።

ይህ ጥቃት በተለያዩ የክልሉ የፍትሕ መዋቅር ውስጥ በመሆን ሕግን እንዲተረጉሙ በተመደቡ ዳኞች ላይ እየተፈጸመ መሆኑን ዳኞችና የክልሉ ፍትህ ቢሮ ማመልከታቸውን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

የክልሉ መንግሥትም ይህንን ድርጊት በሚፈጽሙ ግለሰቦች ላይ አስፈላጊውን ሕጋዊ እርማጃ ለመውሰድ ምርመራ እኣካሄደ መሆኑንም አመልክቷል። (ቢቢሲ አማርኛ)

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

 

በባህሬን የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤት ለመክፈት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ። በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራ የልኡካን ቡድን በሀገሪቱ የኢፌዴሪ የቆንስላ ጽህፈት ቤት መክፈት በሚቻልበት ገዳዮች ዙሪያ ለመምከር ባህሬን ገብቷል። ቆንስላ ጽህፈት ቤቱ የሚከፈተው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በመካከለኛ ምስራቅ ሀገራት ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በቅርቡ በዱባይ ውይይት በሰጡት አቅጣጫ መሰረት እንደሆነ ተነግሯል። (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)
………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኢትዮጵያ እስካሁን የኮሮናቫይረስ አለመከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለፀ። ቫይረሱ ወደ አገር ውስጥ እንዳይገባ ኢንስቲትዩቱ የመከላከልና ክትትል የማድረግ ስራውን አጠናክሮ መቀጠሉንም አስታውቋል።  የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር  ኤባ አባተ (ዶ/ር) ዛሬ የካቲት 24/2012  በሰጡት መግለጫ በሽታው ወደ አገሪቱ እንዳይገባ በመግቢያ በሮች ያሉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል። (ኢቢሲ)


………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኖቭል ኮሮና ቫይረስ በሦስት ተጨማሪ የአፍሪካ አገራት በመስፋፋቱ ቫይረሱ የደረሰባቸውን የአፍሪካ አገራት ቁጥር ወደ ስድስት አሳድጎታል።አሁን ላይ በአፍሪካ ከናይጄሪያ፣ ግብጽ እና አልጄሪያ በተጨማሪ ሞሮኮ፣ በቱኒዚያ እና በሴኔጋል በሚገኙ ታማሚዎች ላይ መገኘቱ ተረጋግጧል። በቅርቡ በሞሮኮ አንድ ከጣሊያን የመጣ የሞሮኮ ዜጋ ቫይረሱ እንደተገኘበት የአገሪቱ መንግሥት ማረጋገጡ ይታወሳል። (ቢቢሲ)


………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ኢትዮ ቴሌኮም ያልተሳተፈበት የኢትዮጵያ ኢንተርኔት ልማት ላይ ያተኮረ ጉባኤ ተካሄደ። ቴሌኮሙ ዘርፉ በቀጥታ የሚመለከተው ተቋም ቢሆንም ምንም አይነት ጥሪ ስላልተደረገለት ሊሳተፍ እንዳልቻለ ተነግሯል። ጉባኤው ላይ በዘርፉ የዳበረ ልምድ ያላቸው የአፍሪካ አገራት ተወካዮች እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተሳታፊዎች መሆናቸው ተግልጿል።በጉባኤው ላይ የኢትዮጵያ የኢንተርኔት ስርፀት 18.6 በመቶ እንደሆነና ይህም ከሌሎች የአፍሪካ አገራት ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ መሆኑ ተነግሯል። (ሸገር ኤፍ ኤም)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ያለ ሕጋዊ ፈቃድ በጎንደር ከተማ የሕክምና አገልግሎት ሲሰጡ ነበር ተብለው የተጠረጠሩ 13 ካናዳውያን በቁጥጥር ሥር ዋሉ። በከተማው ባሳለፍነው ዓርብ የካቲት 20/2012 አንድ የካናዳ ግብረ ሠናይ ድርጅት  13 ሠራተኞቹ ጊዜው ያለፈበትን መድሐኒት ሲያሰራጩ እንደነበር ተጠርጥረው በቁጥጥር መዋላቸውን ዘጋርድን ዘግቧል። ተጠርጠርረው ከታሰሩት መካለም ኹለት ኢትዮጵያውን ሰራተኞች እንደሚገኙበት ተጠቅሷል።የካናዳው ግብረ ሠናይ ድርጅት በበኩሉ  ወደ ኢትዮጵያ ያቀኑት ባለሙያዎች የተማሩ እና ብቃት ያለወቸው መሆኑን በመግለፅ በካናዳ ሲሰጡት ከነበረው የሕክምና አገልገሎት የተለየ አልሰጡም ሲል በድኅረ ገጹ ላይ አስታውቋል። (ዘጋርድያን)

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 በተለምዶ 7ኛ ተብሎ ሚጠራው አካባቢ ልዩ ልዩ የተሰረቁ ንብረቶችን መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስተወቀ ፡፡ የካቲት 19/2012  በህብረተሰቡ ጥቆማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ ኹለት  ልዩ ስሙ ሰባተተኛ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅተው ከሚሰሩበት ኮኒቴነር ውስጥ በቁጥር 203 የአንቴና አናት ፣102 የመኪና ቴፕ፣ የተለያዩ የጎማ መፍቻዎች፣ የኤሌክትሪክ ገመዶች፣ የሰልቫትዮ ኪዳን መያዛቸውን የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበሪያ ሃላፊ ምክትል ኢንስፔክቴር ብርሀኑ አለሙ ተናግረዋል፡፡ (የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት)

 

 

………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትየጰያ ንግድ ባንክ ከሴቶች የቁጠባ ሂሳብ ከ48 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማግኘቱን አስታወቀ።የሴቶች ቁጠባ ሂሳብ አገልግሎት አራት ነጥብ ሶስት ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረጉን የገለጹት የባንኩ ፕሬዝዳንት አቶ ባጫ ጊና፤ ከእነዚህ ደንበኞቹም ከ47 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ መሰብሰቡን አስታውቀዋል።ባንኩ በሴቶች ብቻ አገልግሎት የሚሰጥ የልደታ ቅርንጫፉን ባስመረቀበት ወቅት የባንኩ ፕሬዝዳንት እንዳሉት፤ የሴቶች ልዩ የቁጠባ ሂሳብ በማስከፈት 47 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰብ ችሏል፡፡
እንደ አቶ ባጫ ገለጻ፤ ባንኩ ለሴቶች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ሲሆን ዛሬ የተመረቀው ሴቶች ላይ ብቻ አገልግሎት የሚሰጠው የባንኩ ልደታ ቅርንጫፍ የስራው አንዱ አካል ነው፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here