በከሚሴ ተከስቶ በነበረው ግጭት የተከሰሱ ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ

0
377

በአማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን በከሜሴ የተለያዩ ወረዳዎች ተነስተው በነበሩ ግጭቶች ተከሰው የነበሩ ግለሰቦች ክስ ተቋረጠ፡፡ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ክስ መስርቶባቸው ከነበሩ ከ 80 በላይ ግለሰቦች ውስጥ የእድሜ፣ የጤና እና የወንጀል ተሳትፎን በመመልከት ቁጥራቸው 14 ለሚጠጉ ተከሳሾች ሰኞ የካቲት 30/2012 ክስ አቋርጧል፡፡

በተመሳሳይም በአማራ ክልል በእስር ላይ የነበሩ አምስት የወረዳ አመራሮች ክሳቸው መቋረጡን አዲስ ማለዳ ያገኘችው መረጃ ያሳያል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here