ሊድስታር በ700 ሚሊዮን ብር እስከ መሰናዶ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አስገነባ

0
676

ሊድስታር ኮሌጅ ኦፍ ማኔጅመንት ኤንድ ሊደርሺፕ ከ700 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት ‹‹ካምብድሪጅ አካዳሚ›› የተሰኘ  ከጀማሪ እስከ መሰናዶ የሚያስተምር ትምህርት ቤት አስገነባ።

ኮሌጁ በገመቺስ ደስታ (ቄስ ዶ/ር) የተቋቋመ ሲሆን በቀጣዩ 2013 የትምህርት ዘመንም ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁ ተገልጿል።

በእንግሊዝ አገር ስርዓተ ትምህርትና ከእንግሊዝ አገር ባስመጣቸው የማኔጅመንት ሰዎች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ቅድመ ዝግጅት ማጠቀቁ የተገለጸ ሲሆን፣ ኮሌጁ በአዲስ አበባ ከ25 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ መገንባቱም ከኮሌጁ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ሊድስታር ኮሌጅ ከ2004 ጀምሮ በትምህርትና ተያያዥ ስራዎች ላይ የሰራ ሲሆን በልዩ ልዩ ደረጃ ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here