በአዲስ አበባ ያሉ ኤንባሲዎች አገልግሎት መስጠት እያቆሙ ነው

0
647

በአዲስ አበባ ያሉ የተለያዩ ኤንባሲዎች የኮንሱላር አገልግሎቶቻቸውን ከዛሬ መጋቢት 4/2012 ጀምሮ ማቋረጥ የጀመሩ ሲሆን ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮም አንዳንድ ስብሰባዎቻቸውን ሰርዘዋል፡፡

አዲስ ማለዳ ማረጋገጥ እንደቻለችው የአውሮፓ አገር ኤንባሲዎች አገልግሎቱን መስጠት ካቆሙት መካከል ናቸው፡፡ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮርዳኖስ አለባቸው ለአዲስ ማለዳ እደገለጹት በኢትዮጵያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው ያለመገኘቱን ገልፀው ኤንባሲዎቹ ለምን አገልግሎት እንዳቁሙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

አዲስ ማለዳ በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሷት የምታቀርብ ይሆናል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here