ዳሰሳ ዘ ማለዳ መጋቢት 04/2012

0
1007

 

ዳሰሳ ዘ ማለዳ መጋቢት 04/2012

 

ሁሉም ሰው የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ማድረግ እንደሌለበት ተገለጸ

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ የተከሰተ ሲሆን የአፍ እና የአፍነጫ መሸፈኛ መጠቀም ያለባቸው የጤና ባለሙያዎች፣በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ብቻ እንጂ ሁሉም ሰው መጠቀም እንደሌለበት የጤና ሚኒስትር ሊያ ታደሰ (ዶ/ር) ዛሬ መጋቢት 04/2012 በጽኅፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታወቁ። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኮሮና ቫይረስ በአዲስ አበባ አንድ የጃፓን ዜጋ ላይ መገኘቱን ተከትሎ ሕብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የጤና ሚኒስትሯ ሊያ ታደሰ (ዶ/ር)  አሳስበዋል።

የኮሮና ቫይረስ በአገራችን በመከሰቱ መደናገጥ እና አጉል ፍራቻ ከበሽታው እኩል አደገኛ ሊሆኑ እንደሚችልም ነው  የገለፁት ሚኒስትሯ በበሽታው የተያዘ አብዛኛው ሰው ከቀላል ህመም በኋላ ሙሉ ለሙሉ ይድናል ብለዋል። እድሜያቸው በገፉ ወይንም ተጨማሪ በሽታ ባላቸው ሰዎች ላይ ግን ህመሙ የከፋ ሊሆን እንደሚችል ሊያ ጠቁመዋል፡፡

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በተመሳሳይ ዜና ከኢትጵያ በተቸማሪ በጎረቤት አገራት በሱዳን ኮሮና ቫይረስ የተከሰተ ሲሆን አንድ ግለሰብብ በትላንትናው ዕለት በቫይረስ ሕይወቱ ማለፉን የአገሪቱ የጤና ሚኒስቴር ማስታወቁን አልአረቢያ ዘግቧል።በኬንያም ኮሮና ቫይረስ መግባቱ ተገልጿል።(ቢቢሲ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በአዲስ አበባ ያሉ የተለያዩ ኤንባሲዎች የኮንሱላር አገልግሎቶቻቸውን ከዛሬ መጋቢት 4/2012 ጀምሮ ማቋረጥ የጀመሩ ሲሆን ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮም አንዳንድ ስብሰባዎቻቸውን ሰርዘዋል፡፡አዲስ ማለዳ ማረጋገጥ እንደቻለችው የአውሮፓ አገር ኤንባሲዎች አገልግሎቱን መስጠት ካቆሙት መካከል ናቸው፡፡ የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮርዳኖስ አለባቸው ለአዲስ ማለዳ እደገለጹት በኢትዮጵያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው ያለመገኘቱን ገልፀው ኤንባሲዎቹ ለምን አገልግሎት እንዳቁሙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡(አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

ሰሞኑን በአብዛኛዎቹ የአገሪቱ ክፍሎች እየተስተዋለ ያለው ወበቅ በልግ ወቅት የሚከሰት እንደሆነ እና በቀጣዮቹ ሳምንታት የበልግ ዝናብ በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች እንደሚጠበቅ የብሔራዊ ሚትዮሮሎጂ ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

በበልግ ወራት ወደ አገሪቱ በሚገባው እርጥበት አዘል አየር የሚፈጥረው ደመና፣ የፀሐይ ጨረር መሬት ደርሶ ወደላይ ሲመለስ እንዲታመቅ ስለሚያደርገው በአካባቢው ወበቃማ እና ምቹ ያልሆነ አየር እንዲኖር እንደሚያደርግ የአየር ፀባይ እና የአየር ሁኔታ ትንበያ ባለሙያ የሆኑት  ታምሩ ከበደ ገልጸዋል፡፡ከመጋቢት እስከ ግንቦት ባሉት ወራት በተለይ ደግሞ በመኝታ ሰዓት ምቾት የሚያሳጣ የአየር ሁኔታ በብዛት የሚስተዋልበት እንደሆነም ባለሞያው ጠቅሰዋል፡፡(ኢቢሲ)

 

 

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here