ሃሌሉያ ሆስፒታል አራት ኪሎ የሚገኘው ቅርንጫፉን ለኮቪድ 19 ተጠቂ ታማሚዎች ማቆያ ሊያደርገው ነው

0
1171

የሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ኪሎ የሚገኘው ቅርንጫፉን በኮቪድ 19  ኮሮና ቫይረስ ለተጠቁ ፅኑ ህሙማን ማቆያ እንዲሆን ከመንግሥት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገለጸ።

ዛሬ መጋቢት 10/2012 በሆስፒታሉ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው በቫይረሱ ምልክት የታየባቸውን ተጠቂዎች በለይቶ ማቆያ ከፍል በማኖር እንዲሁም ቫይረሱን ለመቆጣጠር መንግስት ላቋቋመው ግብረ ሃይል መረጃ በመስጠት እየሰራ መሆኑ አስታውቋል።

በሆስፒታሉ ከፍተኛ የሳምባ ስፔሻሊስት የሆኑት ጌታቸው አደራዬ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ እስካሁንም ስድስት የኮሮና ቫይረስ ምልክት የታየባቸውን ሰዎች ለግብረ ሃይሉ እንዳስተላለፉ ተናግረዋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here