ዳሰሳ ዘ ማለዳ (መጋቢት 10/2012)

0
921

የጋራ መኖሪያ ቤቶች የውል ስምምነት የወሰን ወዝግብ ያለባቸውን ቤቶች እንደማያካትት ተገለጸ

በ13ኛው ዙር እጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየተከናወነ ያለው የውል ስምምነት የወሰን ውዝግብ ያለባቸውን ቤቶች እንደማያካትት ተገለፀ። ሰሞኑን በተለያየ የግል ምክንያት እጣ ወጥቶላቸው ውል ያልተፈራረሙ እድለኞችን ውል የማፈራረም ስራ እተከናወነ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ጸሕፈት ቤት፣ ቤቶቹን የማስተላለፍ አካል የሆነው የውል ሰምምነትም በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መካከል የወሰን ጥያቄ የተነሳባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች እንደማያካትት አስታውቋል። (ከንቲባ ጽሕፈት ቤት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የኢትዮጵያ ሐምሊን የፌስቱላ ሆስፒታል እና የካትሪን ሐምሊን የፌስቱላ ፋውንዴሽን መስራች  ካትሪን ሐምሊን(ዶ/ር) ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ካትሪን ሐምሊን በ96 ዓመታቸው በትናንትናው እለት ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ተገልጿል። ካትሪን ሀምሊን ፌስቱላ ኢትዮጵያ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት በማቋቋም ከ60 ዓመት በላይ የፌስቱላ ህክምናን የሰጡ ሲሆኑ በበጎ ተግባር ላይ ተሰማርተው የበርካታ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ችግርን የቀረፉ በመሆናቸው የኢትዮጵያ የክብር ዜግነት እና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የክብር ዶክትሬት ተበርክቶላቸዋል።(ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የሃሌሉያ አጠቃላይ ሆስፒታል አራት ኪሎ የሚገኘው ቅርንጫፉን በኮቪድ 19  ኮሮና ቫይረስ ለተጠቁ ፅኑ ህሙማን ማቆያ እንዲሆን ከመንግሥት ጋር እየተነጋገረ መሆኑን ገለጸ።ዛሬ መጋቢት 10/2012 በሆስፒታሉ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንዳስታወቀው በቫይረሱ ምልክት የታየባቸውን ተጠቂዎች በለይቶ ማቆያ ከፍል በማኖር እንዲሁም ቫይረሱን ለመቆጣጠር መንግስት ላቋቋመው ግብረ ሃይል መረጃ በመስጠት እየሰራ መሆኑ አስታውቋል።በሆስፒታሉ ከፍተኛ የሳምባ ስፔሻሊስት የሆኑት ጌታቸው አደራዬ (ፕሮፌሰር) እንደተናገሩት፣ እስካሁንም ስድስት የኮሮና ቫይረስ ምልክት የታየባቸውን ሰዎች ለግብረ ሃይሉ እንዳስተላለፉ ተናግረዋል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

በሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በኮሮና ቫይረስ ጥርጣሬ በለይቶ ማቆያ ገብተው የነበሩ 30 የውጭ ሀገራት ዜጎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ገለጸ። በሽታው ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ተጋላጭ እንዳይሆን ጥንቃቄ እየተደረገ ነው ሲሉም ጤና ቢሮው ጤናና የጤና ነክ ድንገተኛ አደጋዎች ቅኝትና ምላሽ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት  እንዳሻው ሽብሩ ገልጸዋል  ።

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የኤልክትሪክ ኃይል ስርቆት ወንጀል መፈፀማቸው የተረጋገጠባቸው 18 ግለሰቦች ከ2 አስከ 10 ዓመት በሚደርስ እስር የተቀጡ ሲሆን ወንጀለኞቹ ባለፉት ስድስት ወራት በሕገ-ወጥ መንገድ፣ ከማብራት ኃይል እውቅና ውጭ ከኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ላይ ገመድ በመቀጠል የኤልክትሪክ ኃይል ስርቆት ወንጀል ሲፈፅሙ የቆዩ መሆናቸውን የአገልግሎቱ የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ለኢቲቪ ገልፀዋል።

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

ከኮቪድ19 ጋር በተያያዘ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 925 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን የአማራ ክልል ንግድና ልማት ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን አንዳንድ የንግድ ተቋማት አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል። እስካሁን በክልሉ በተደረገ የቁጥጥር ስራም በተለያዩ ሸቀጦች ላይ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 925 የንግድ ተቋማት መታሸጋቸውን ተነግሯልል። ከድርጊቱ ጋር በተያያዘም 16 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል።(ኢቲቪ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

ትምህርት ሚኒስቴር የፈተና ወቅትን በተመለከተ መርሃ-ግብሩን ወደፊት እንደሚገልጽ ሚንስትር ጌታሁን መኩሪያ(ዶ/ር) ዛሬ መጋቢት 10/2012 በጽኀፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መርሃግብር ወደፊት እንገልፃለን ብለዋል። ሚኒስትሩ አክለውም ተፈታኞች በተዘጉት የትምህርት ቀናት በቤታቸው ዝግጅታቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አሳስበዋል። መንግሥት የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እስከ መጋቢት 21/2012 ዓ.ም ድረስ ለ15 ቀናት ትምህርት ቤቶች እንዲዘጉ ማድረጉን አስታውሰው በዚህ ወቅት ሳይሰጥ የቀረውን ትምህርት በተመለከተ ማካካሻ ትምህርት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።(ቢቢሲ አማርኛ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………….

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጉን ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቢ ሳኖ ዛሬ መጋቢት 10/2012  በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ባንኩ የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው የኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ የከፋ ጉዳት እንዳያደርስ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ነው ብለዋል። (ጤና ሚኒስቴር)

 

 

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here