የፋናው ጋዜጠኛ በኮቪድ19 ምክንያት ራሱን ለይቶ ማቆያ አስገባ

0
907

 

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋዜጠኛ በኮቪድ19 ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው ተብሎው ከተጠረጠሩ ግለሰቦች መካከል በመሆኑ ከጤና ሚኒስቴር ትላንት ማምሻውን በተገለጸለት መሠረት ከዛሬ መጋቢት 11/2012 ከጠዋት ጀምሮ በመኖሪያ ቤቱ እራሱን ለይቶ ማቆየት ጀመረ።

ጋዜጠኛው ከአንድ ተራድኦ ድርጅት ጋር በነበረው የሥራ ግንኙነት ለበሽታው ሊጋጥ የሚችልበት ዕድል እንዳለ በመገመቱ ነው ራሱን እንዲለይ የተደረገ ነው ሲሉ በፋና ያሉ ምንጮች ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

ግለሰቡ ምንም ዓይነት የበሽተው ምልክት ያላሳየ እና  እስከ ትናትናው እለት ድረስ በስራ ገበታው ላይ የቆየ ሲሆን ጋዜጠኛውን ለማነጋገር በተደጋጋሚ ብንሞክርም ለማግኘት አልቻልንም።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here