ዳሰሳ ዘ ማለዳ (መጋቢት 11/2012)

0
509

በኮቪድ 19 ምክንያት በማረሚያ ቤት ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰ እና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ተወሰነ

በማረሚያ ቤቶች፣ ቫይረሱ ከገባ ለቁጥጥር አስቸጋሪ ሁኔታ የሚፈጠር በመሆኑ ህጻናትን የያዙ፣ የአመክሮ ጊዜያቸው የደረሰና ቀለል ያለ ክስ ያለባቸው እንዲለቀቁ መወሰኑንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ አስታወቁ።

የእምነት ተቋማትም እንደ የአምልኳቸው ሁኔታ ለቫይረሱ ስርጭት ምቹ ሊሆኑ ስለሚችሉ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲያሳልፉም ከስምምነት መደረሱን ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል። (ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ዳሽን ባንክ በኮቪድ-19 ምክንያት የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ አደረገ ባንኩ ቫይረሱን ለመከላከል በሚሰጠው አገልግሎት የሰዎችን ንክኪ ለመቀነስ የሚያስችል እርምጃ መውሰዱን ስታወቀ ሲሆን ከመጋቢት 14/2012 ጀምሮ ለተከታታይ 60 ቀናት ተግባራዊ የሚሆን የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያዎችን አድርጓል።ደንበኞች ወደ ቅርንጫፍ ባንኮች ሳይሔዱ በቪዛ እና በወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት የክፍያ ካርዶች ከኤቲኤም በየቀኑ የሚፈልጉትን የወጪ ገንዘብ መጠን ገደብ ከ5 ሺህ ወደ 10 ሺህ ብር ከፍ እንዲል አድርጓል። (አዲስ ማለዳ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ባለሥልጣን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ትርፍ የሚጭኑ ባለታክሲዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ገልጿል። ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ የሕዝብ አገልግሎት ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እና ባለታክሲዎች መጨናነቅ እንዳይፈጥሩ መመሪያ ተላልፎላቸው መመሪያውን ጠብቀው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የተነገረ ሲሆን፣ አሠራሩን የአውቶቡስ አገልግሎት ሰጪዎች ተግባራዊ ቢያደርጉትም ታክሲዎች እና ሚኒባሶች ሕጉን እያከበሩ አለመሆኑ ተገልጿል።

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ለኮቪድ19  መከላከያ 20 ሚሊየን ብር የመደበ ሲሆን የማህበሩ ዋና ፀሃፊ መሸሻ ሸዋረጋ (ዶ/ር) ማህበሩ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚውል 20 ሚሊየን ብር መመደቡን አስታውቀዋል። ማህበሩ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ከዓለም አቀፉ የቀይ መስቀልና ቀይ ጨረቃ ፌዴሬሽን እንዲሁም ከእህት ማህበራት ጋር በመሆን የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን በመግለጽ በዚህም 5 ሺህ የፊት መሸፈኛ ማስኮች፣ 6 ሺህ የሰርጅካል ጓንቶችን፣ 1 ሺህ 500 የህክምና ጫማዎች፣ 1 ሺህ የፕላስቲክ የፊት መከላከያ እና 5 ሺህ የመለያ ገዋኖችን ለመግዛት መታቀዱንም ገልጸዋል።(ኢዜአ)

 

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በአዲስ አበባ ዛሬ መጋቢት 11/2012 ሌሊት በደረሱ የእሳት አደጋዎች 2 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር መውደሙን የእሳት እና የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን  አስታውቃል።አደጋው በንፋስ ስልክ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጎፋ ገብርኤል አካባቢ ባለ ጋራዥ ቤት የተፈጠረ ሲሆን በአደጋው 2 ነብ 5 ሚሊዮን ብር ወድሟል። አደጋውን ለመቆጣጠር ለአምስት ሰዓት እልክ አስጨራሽ ትግል መካሄዱን ኮሚሽኑ ገልጿል።በተደረገው ርብርብም 30 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ማዳን ተችሏል ተብሏል።(ኢትዮኤፍኤም)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

ዓይነ ሥውራን ለኮቪድ- 19 ለመሳሰሉ በንክኪ ለሚተላለፉ በሽታዎች ተጋላጭ ብንሆንም፣ መንግሥት እስካሁን ድጋፍ እያደረገልን አይደለም ሲል የኢትዮጵያ ዓይነ ሥውራን ብሔራዊ ማኅበር ገለጸ።አብዛኛዎቹ አባሎቻችን የድሀ ድሀ ስለሆኑ የንጽሕና መጠበቂያዎችን ማሟላት አይችሉም መንግሥትን ድጋፍ ጠይቀን ምላሽ እየጠበቁ ነው ሲሉም የማሕበሩ ሥራ አስኪያጅ ሡልጣን ይስሙ ተናግረዋል። (ኢቲቪ)

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ግለሰብ ከዛሬ ሳምንት መጋቢት 04/2012 ይፋ ከተደረገ በኋላ በሽታው የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር ዘጠኝ መድረሱን የጤና ሚኒስትር ገለጸ። ዛሬ መጋቢት 11/2012 እንደተገለጸ  በሽታው ከተገኘባቸው ተጨማሪ ሦስት ሰዎች መካከል አንደኛው የ44 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ጃፓናዊ፣ ሌላው የ39 ዓመት ኦስትሪያዊ፣ እንዲሁም ሦስተኛዋ ደግሞ የ85 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋ ኢትዮጵያዊት መሆናቸው ተገልጿል። እስካሁን በሽታው እንዳለባቸው ከተረጋገጡት ሰዎች አራቱ ጃፓናዊያን፣ ሶስቱ ኢትዮጵያዊያን፣ አንዷ እንግሊዛዊት እና አንዱ ኦስትሪያዊ ናቸው።(ጤና ሚኒስቴር)

 

…………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………………

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮቪድ 19  በከተማዋ መታዩቱን ተከትሎ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ችግር እንዳይፈጠር ግብረ ሃይል በማቋቋም የንግድ እንቅስቃሴ ላይ ቁጥጥር እያደረገ እንሚገኝ የገለጸው ቢሮው እስከ ዛሬ ድረስ ከ14 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ ቁጥጥር እና ክትትል መደረጉን የከተማ አስተዳደሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት በመረጃው አመላክቷል።በቁጥጥሩም 11 የምርት አይነቶች እና 12 ፋርማሲዎችን ጨምሮ በ767 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ የቢሮ ኃላፊ አብዱልፈታ የሱፍ ተናግረዋል።(ኢቲቪ)

 

 

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here