10 ቱ ዓለምን ያስጨነቁ አስከፊ ወረርሽኞች

0
614

ምንጭ፡ – – ቪዥዋል ካፒታሊስት (2020)

ዓለማችን በየጊዜው የተለያዩና ከባድ የሆኑ ወረርሽኞችን አስተናግዳለች። ከዚህም ውስጥ ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበው ‹ጥቁር ሞት› ተብሎ በተሰየመና፣ ከአይጦችና ነፍሳት በቁንጫ በኩል ወደ ሰዎች የተላለፈው በሽታ ነው። ይህም ከ1347 እስከ 1351 ለአምስት ዓመታት የዘለቀ ወረርሽኝ ሲሆን፣ አውሮፓ ከዚህ በሽታ ለማገገም 200 ዓመታት እንደወሰዱባት ይነገራል።

ፈንጣጣ በተመሳሳይ ከፍተኛ እልቂት የተመዘገበበት ሲሆን፣ ጀስቲንያን የተባለው ወረርሽኝ ከ541 እስከ 542 የተከሰተ ነው። ይህም በጊዜው በነበረው ጀስቲንያን ግዛት ምክንያት ሥሙን ያገኘ ከመሆኑ ባሻገር፣ የባዛንታይንን ግዛት በእጅጉ የፈተነ እንደነበር ይነገርለታል።

ኤች አይ ቪ ኤድስ ባከተለው ሞት ብዛት በአምስተኛነት ሲከተል፣ ከቻይና የተነሳውና ሦስተኛው ወረርሽኝ (The third plague) የሚል ሥም የተሰጠው ወረርሽኝ፣ ከ‹ጥቁር ሞት› እና ከ‹ጀስቲንያን ወረርሽኝ› ቀጥሎ በተከታታይ ከፍተኛ ሞት ያስከተለ ስለነበር ነው ‹ሦስተኛው› የሚል ሥያሜ የተሰጠው።

እነዚህ ወረርሽኞች በሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ የሞተባቸው ናቸው። በተጓዳኝ ግን በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ሕዝብ የሞተባቸው ስዋይን ፍሉ፣ ቢጫ ወባ እና ኢቦላም በዚህ ተጠቃሽ ናቸው። አሁን ላይ ዓለምን እያስጨነቀ የሚገኘው ኮቪድ19 ኮሮና ቫይረስም አሁን ባለበት ደረጃም እነዚህን ዓለምን ያስጨነቁ ወረርሽኞችን መቀላቀል ችሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 72 መጋቢት 12 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here