በኢትዮጵያ በኮቪድ19 የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው ተገኘ

0
815

ከመጋቢት 3/2012 የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በአገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው መገኘቱ ተገለጸ።

በዚህም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር አስራ ኹለት መድረሱን የጤና ሚኒስቴር  ያስታወቀ ሲሆን   ቫይረሱ የተገኘበት ታማሚ የ 34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከዱባይ ወደ አገር ውስጥ መጋቢት 10/2012  የገባ እንደሆነም ተነግሯል።

ግለሰቡ የህመም ምልክት የነበረው በመሆኑ በመጋቢት 13/2012 ወደ ጤና ተቋም የሄደ ሲሆን ተቋሙም ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማደረግ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የህክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛልም ተብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ ይገኛሉ።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here