ኦነግ እና ኦፌኮ የምርጫውን መራዘም ተቃወሙ

0
461

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) እና የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አርብ፣ መጋቢት 25 ባሰራጩት የጋራ መግለጫ የ2012 ምርጫ መዘዋወርን በተመለከተ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣው መግለጫ ላይ ተቃውሞ አለኝ ሲሉ ገልጸዋል። ይሁንና የምርጫው መራዘምን አስመልክቶ ሁሉን ባለድርሻ አካላት ያካተተ ንግግር እና ስምምነት ላይ ለመድረስ እንደ መልካም አጋጣሚ መጠቀም ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ኹለቱ ፓርቲዎች በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በአንድ ላይ የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት ቅድሚያ እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል። ይሁንና ወረርሽኙን እንደሰበብ ተጠቅሞ የፖለቲካ ምኅዳሩን የበለጠ በማጥበብ እና እንዲባባስ በማድረግ ብሔራዊ ምርጫውን ማራዘም ተገቢ አይደለም ሲሉ መግለጫቸውን ደምድመዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዚህ ሳምንት ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ መጪውን ምርጫ በታቀደው የጊዜ ሰሌዳ ማካሔድ እንደማይችል ገልጾ የጊዜ ሰሌዳውን ሰርኦ ሁሉንም እንቅስቃሴዎች እንዳቋረጠ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ ቦርዱም አዲስ የምርጫ ማካሔዳ ቀን ወረርሽኙ ሲያልፍ ይሰጣል ሲል አስታውቋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here