ኮሮናና ፖለቲከኞቻችን

0
917

በያዝነው ሳምንት ከኮቪድ19 ወረርሽን ጋር በተያያዘ የአገራችን የተለያዩ ክልሎች የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ይበጃል ያሉትን ወሳኔዎችን አሳልፈዋል።በትግራይ፣ አማራ፣ አሮሚያ እና ደቡብ ክልሎች የተለያዩ ውሳኔዎችን ያሳለፉ ክልሎች ሲሆን ከወሰኗቸው ወሳኔዎች መካከል ደግሞ የሕዝብ ትራስፖርት በክልላቸው እንዳይንቀሳቀሱ ማገድ እና መከልከልን ይጨምራል። ምንም እንኳን አንዳንድ ወሳኔዎቻቸው ምነው በድንገት ሆነ መናገር አልያም መጠቆም ያስፈልግ እንደነበርም ከብዙዎች አስተያየት ለመታዘብ ችለናል።
ከቫይረሱ ጋር በተያያዘም እስከ አሁን ይህ ጽሁፍ እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ በቫይሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደርሷል ሦስት ሰዎች ደግሞ አገግመዋል። ይህን ተከትሎም ተቋማት ሰራተኞቻቸውን ቀንሰው እቤታቸው እንዲሰሩ ማድረጋቸውን ቀጥሏል። ቫይረሱን ለመከላከለ እና ለመቆጣጠርም የግል፣የሃይማኖት እና ሌሎችም ተቋት የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገፍተውበታል።
በዚህ ሳምንት በማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ሲነገረ የነበረው ጉዳይ ከውጭ የመጡ ሰዎች ከማቆያ እየወጡ መሆናቸውን ፖሊስ መረጃው እንደደረሰው እና ለዚህም እርምጃ እንሚወስድ መናገሩ በሰፊው መነጋሪያ ሆኖ ነበር። ድርጊቱም በሰው ሕይወት ላይ መቆመር እንደሆነ የገለጹት አስተያየታቸውን በማህበራዊ ገጻቸው ላይ ያሰፈሩት ሰዎች መንግስትም ይሁን ሌሎች ሰዎች ችግሩን እንፍታ ጎበዝ ይህ እኮ ከባዱ አደጋ ነው ያሉ ሲሆን ሌሎች ደገሞ ሙስና አሁንም አልቀነሰም እንደው በኮሮና ላይ ራሱን እየገለጠ እንሆነ በመለግለፅ ይህም በሥነ ምግባራችን ምን ያህል እንደወረድን ማሳያ ነው ሲለ አስተያየተቸውን አስፍረዋል።
የኮሮና ቫይረስ ይዞት የሚመጣው መመዙ ብዙ እንደሆነ ከእለት እለት እየሰማን እና እያየነው ያለነው ነገር በቂ ምስክር ሊሆን ይችላል። አሁንም ድረስ ስለ ቫይረሱ ያልሰሙ የሚመስሉ ብዙ ሰዎች እንዳሉ እያየን ሲሆን ምን ያህል አስጨናቂ መሆኑንም እኔ ጋር ካልደረሰ አልገነዘበውም ያሉ የሚመስሉ ሰዎች እንዳሉም በማህበራዊ ሚዲያዎች እቃ ለመግዘት፣ለታክሲ የተሰለፉ ሰዎችን የሚያሳዩ ፎቶዎች በቂ ምስክር ናቸው።
መንግስታዊ ተቋማት የሃይማት እና ግል ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት ሠራተኞቻቸው እንዲያርፉ እና ቤታቸው እንዲሰሩ በማድረግ ባስ ሲሊም አንዳንድ የንግድ ድርጅቶች እስከመዘጋት ደርሰዋል ቫይረሱን ለመካከል እና ለመቆጣጠር ሲሉ።
ሌሎች እንደ የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ያሉ ድርጅቶች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ሥራቸው እንደ ተስተጓጎለ እና በያዝነው 2012 ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው አገር አቀፍ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተፅዕኖው የጎላ ሆኑ በመገኘቱ ሥራውን ፈታኝ እንዳደረገበትም በዚህ ሳምንት ነበር በማሕበራዊ ገጹ ላይ እወቁልኝ ሲል ያስታወቀው ።ይህ በመሆኑም አንዳንድ ፖለቲከኞች ይህ የሆነው ሆን ተብሎ የሚል እምነት እንዳለወች ሃሳባቸውን ሰንዝረዋል እንዲ ብለው አስተያታቸውንም ሰጥተዋል ‹‹አሁን በስልጣን ላይ ያለኸው መንግስት ሆይ እንኳን ደስ አለህ›› ማለታቸውን ተከትሎም ብዙዎች በማሕበራዊ ሚዲያዎች ሃሳባቸውን አስፍረዋል።
ምነው እነኚ ፖለቲከኞቻችን ሰከን ብትሉ ለመምረጥ እኮ ጤነኛ መሆን ያስፈልጋል ስለዚህ ለማውራትም ጊዜውም አይደለም ብለው ብዞዎች ሃሳባቸውን አጣጥለውባቸዋል።
ስለሆነም ጠቢቡ ሰለሞን ለሁሉም ገዜ አለው እንዳለው እባካቸሁ አንዳንድ ፖለቲከኞቻችን ዝም ማለት ባለባቸሁ ጊዜ እንኳን ዝም በሉ አለበለዚያ ግን ታዛቢው ብዙ ነውና ነጥብ እንዳትጥሉ መጠንቀቅ ይኖርባችኋል ብለው መልዕክታቸውንም አስተላልፈውላቸዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 74 መጋቢት 26 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here