በኢትዮጵያ በቀጣይ ሦስት ወራት 2 ሚሊዮን ሰዎች ከሥራ ይፈናቀላሉ ተባለ

0
832

በኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በኢትዮጵያ በቀጣይ ሦስት ወራት 2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከሥራ ገበታቸዉ ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኤፍሬም ተክሌ (ዶ/ር) ገለጹ።

በቫይረሱ ወረርሽኝ መሥፋፋት ምክንያት ሊፈናቀሉ ይችላሉ ከተባሉት መደበኛ ሠራተኞች በተጨማሪ 1.9 ሚሊዮን የሚሆኑ በጊዜያዊነት ኑሯቸዉን የሚመሩ ዕለታዊ ሠራተኞች ሥራ አልባ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሎ እንደሚገመትም ተገልጿል።

ኮሚሽነሩ “የኮሮና ቫይረስ ኢኮኖሚ ተጽዕኖ በኢትዮጵያ” በሚል ርዕስ ኀሙስ፣ ሚያዚያ 1/2012 በተዘጋጀ መድረክ ላይ ከገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ተካልኝ ቶሊና (ዶ/ር) እና ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፍ ኀላፊዎች ጋር ባደረጉት የቪዲዮ ውይይት ላይ የኮረና ቫይረስ በአገሪቱ ሊመጣ የሚችለውን የአጭርና የረጅም ጊዜ ተጽዕኖ አብራርተዋል፡፡

እንደ ኮሚሽነሩ ገለጻ የኮረና ቫይረስ በአገሪቱ አሁን ባለበት ሁኔታ የሚገታ ከሆነ በአጭር ጊዜ ተጽዕኖው 800 ሺሕ ሰዎች፣ በመካከለኛ ተጽዕኖው 1.4 ሚሊዮን ሰዎች እንድሁም የቫይረሱ ሥርጭት በዚሁ ከቀጠለ 2 ሚሊዮን ሰዎች በቀጣይ ሦስት ወራት ከሥራ ገበታቸው ሊፈናቀሉ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ኮሚሽነሩ አክለውም ቫይረሱ ወረርሽኝ ከሚቀጥሉት ሦስት ወራት ከዘለለ የሥራ አጥ ቁጥሩ በእጥፍ ሊጨምር እንደሚችልም ጠቁመዋል፡፡

ቅጽ 2 ቁጥር 75 ሚያዝያ 3 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here