አማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር የአክሲዮን ሽያጩን አራዘመ

0
1301

በምሥረታ ላይ የሚገኘው የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ከሚያዝያ 8/2012 ጀምሮ ላልተወሰነ ጊዜ የአክሲዮን ሽያጩን ማራዘሙን ሚያዚያ 7/2012 በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።
ባንኩ በምሥረታ ሂደት ላይ ሲሆን ከነሐሴ 11/2011 ጀምሮ አክሲዮን ሲሸጥ የቆየ ሲሆን፣ እስከ አሁን 6 ቢሊዮን ብር የአክሲዮን ሽያጭ መፈረሙንና ከዚህ ውስጥም ከ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ መከፈሉን ገልጿል።
ማኅበሩ እስከ አሁን ያከናወነው የአክሲዮን ሽያጭ ስድስት ቢሊዮን ብር መደርሱን አስታወቆ፣ እስከ አሁን በተሸጠው አክሲዮን ላይ ከ128 ሺሕ በላይ ሰዎችም አክሲዮን መግዛታቸውንም አያይዞ ጠቅሷል።
ከዚህ በፊት አክሲዮን በመግዛት ያልተሳተፉ ካሉ ጊዜው በመራዘሙ ዕድሉን እንዲጠቀሙበት የአማራ ባንክ አክሲዮን ማኅበር ፕሮጀክት ማናጀር መሰንበት ሸንቁጤ አሳስበዋል። የአክሲዮን ሽያጩ በተራዘመበት ጊዜ ባንኩ ዘመናዊ አሠራሮችንና ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም የሚያስችሉ ተግባራትን ሲሠራ እንደሚቆይም አስታውቀዋል።
የባንኩ አክሲዮን ሽያጭ የዲያስፖራው ኅብረተሰብ ክፍል እንዲሳተፍ የሚፈቅደው የብሔራዊ ባንክ መመሪያ ዘግይቶ መድረሱን ተከተሎ፣ ከዚህ በፊት የአክሲዮን ሽያጭ ጊዜውን ማራዘሙ የሚታወስ ነው።

ቅጽ 2 ቁጥር 76 ሚያዝያ 10 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here