ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጣቸው አገልግሎቶች ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ

0
311

ኢትዮ ቴሌኮም በሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ላይ ማማሻያና የዋጋ ቅናሽም ማድረጉን አስታውቀ።
የተደረገው የቅናሽ ማሻሻያ የሞባይል ድምጽና የኢንተርኔት ጥቅልን ያካተተ ሲሆን፣ በአምስት ብር የ30 ደቂቃ ድምጽና 20 ነፃ አጭር የጽሑፍ መልዕክት አንዱ ነው። በዚህም የተደረገው ቅናሽ ከዚህ ቀደም ከነበረው የ53 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል።
ኹለተኛው በ5 ብር 100 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር የጽሑፍ መልዕክት ወይም በ10 ብር 250 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 የአጭር የጽሑፍ መልዕክት ነው። ይህም ከቀድሞ ጋር ሲነጻጸር የ56 በመቶ ቅናሽ አለው።
እንዲሁም በ15 ብር 30 ደቂቃ የድምጽ፣ 300 ሜጋ ባይት የኢንተርኔት ዳታና 20 አጭር የጽሑፍ መልዕክት በአንድነት ይህም ከቀድሞው አንጻር የ45 በመቶ ቅናሽ ያለው መሆኑን ኢትዮ ቴሌኮም በመግለጫው አስታውቋል።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ ሚያዚያ 7/2012 በሰጡት መግለጫ፣ ዜጎች እንቅስቃሴያቸውን በመገደብ በቤታቸው እንዲቆዩ በማድረግ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ ማሻሻያ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
የተደረገው ማሻሻያ በጥቅሉ ‹በቤትዎ ይቆዩ› የሞባይል ጥቅል አገልግሎት፣ የተለያዩ ድረ ገጾችን በነጻ መጎብኘት የሚያስችል አገልግሎት እንዲሁም የቅድመ ክፍያ ሞባይል አየር ሰዓት የቆይታ ጊዜን የሚያራዝም አገልግሎት ነው። ይህም ከመጋቢት 8/2012 ጀምሮ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሏል።
አገልግሎቱን የሚጠቀሙ ደንበኞች መሻያ የተደረገባቸውን አገልግሎቶች ከማለዳው 12 ሰዓት እስከ ቀኑ 10 ሰዓት ድረስ መጠቀም የሚችሉ ሲሆን፣ ከተጠቀሰው ሰዓት ውጭ ግን በነበረው መደበኛ ታሪፍ አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ቅጽ 2 ቁጥር 76 ሚያዝያ 10 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here