የሚንስትሮች ምክር ቤት አዳዲስ እርምጃዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

0
708

የሚንስትሮች ምክር ቤት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ በአገር ምጣኔ ሀብት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቀነስ መወሰድ የሚገባቸውን እርጃዎች በተመለከተ ተወያይቶ ማሳለፉ ተገለፀ። ተከሰተው የምጣኔ ሀብት መቀዛቀዝ አብዛኛውን የሕብረተሰብ ክፍል እንደሚጎዳ ታሳቢ በመደረጉ መንግሥት ዘርፈ ብዙ ድጋፎችን ለኅብረተሰቡ እያደረገ እንደሚገኝ ተጠቅሷል። ይሁን እንጂ ከመንግሥት የሚደረገው ድጋፍ ባሻገር ለንግዱ ማኅበረሰብ እና ድጋፍ ለሚያደርጉ ዘካላት ማበረታቻ የሚሆኑ  አንዳንድ ውሳኔዎች ተላልፈዋል።

በዚህም መሰረት የገንዘብ ድጋፍ የሚያደርጉ ዜጎች እንዲበረታቱ በጎ አድራጊዎች ለመንግስት የሚያደርጉት የገንዘብ ድጋፍ ግብር ከሚከፈልበት የ2012 ለግብር ክፍያ ላይ የ20 በመቶ ያልበለጠ ተቀናሽ ማድረግን፣ የተጨማሪ እሴት ታከስ እና ተርን ኦቨር ታክስ የሚያስታውቁበት እና የሚከፍሉበት ጊዜ በአንድ ወር እንዲራዘም ማድረግን፣ የንግድ ድርጅቶች በስራ ላይ በቆዩባቸው ጊዜያት ያጋጠማቸው ኪሳራ ማሸጋገርን፣ በስራ መቀዛቀዝ ምክንያት የጡረታ መዋጮን ለመክፈል የተቸገሩ አሰሪዎች የሚቀጥሉትን ሶስት ወራት የጡረታ መዋጮ ሂሳብ ከሚጠበቅበት ከሀምሌ 1 ቀን 2012 ጀምሮ እንዲከፍሉ የክፍያ ሽግሽግ ማድረግን በተመለከተ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማስፈፀሚያ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ላይ በመወያየት ስራ ላይ እንዲውል ወስኗል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here