“ኮቪድ19 ምርጫን ማራዘም እና የህግ አማራጮች” በሚል ርዕስ ዛሬ ሚያዚያ 21/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የተለያዩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የተሳተፉበት ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉትም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ጋር በኮቪድ19 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ምክክሮችን ስናካሂድ ቆይተናል፡፡ ምክክራችንን በመቀጠል፣ ዛሬ ጠዋት ቀጣዩን ምርጫ ለማካሄድ የሚቻልባቸው ሕገ መንግሥታዊ አማራጮችን በተመለከተ ውይይት አድርገናል፡፡ እንዲህ ያሉት ውጤታማ ውይይቶች የኢትዮጵያን የዴሞክራሲ ጉዞ በእጅጉ የሚደግፉ ናቸው በማለት ከውይይቱ በኋላ በፌስቡክ ገፃቸው አስፍረዋል፡፡







