ጀርመን የ4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለኢትዮጵያ ለመስጠት ቃል ገባች

0
713

ጀርመን የኮሮና ቫይረስ ሥርጭት የፈጠረውን ምጣኔ ሀብታዊ ቀውስ ለመቅረፍ የሚውል የ4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ለኢትዮጵያ ልትሰጥ ነው። የጀርመን የምጣኔ ሀብት ትብብር እና ልማት ሚኒስትር ጌርድ ሙይለር ይኽንኑ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ማረጋገጣቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ሚያዚያ 22/2012 አስታውቋል።
ከጀርመን ይገኛል የተባለው 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ለሦስት ዐበይት ጉዳዮች የሚውል መኾኑም የተጠቀሰ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን አጠቃላይ ምጣኔ ሀብት ለማረጋጋትና ለመደገፍ፣ በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ የሥራ ዋስትና እንዲረጋገጥ ለማስቻልና ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር የጤና ግብዐቶችን ለመግዢያ እንዲውል ለማስቻል መሆኑ ተገልጿል።
ድጋፉ የሚደረገው ኢትዮጵያ እና ጀርመን ትብብራቸውን ለማደስ ታኅሣሥ ወር ላይ በገቡት ቁርጠኝነት መሠረት ነው ሲል ኤምባሲው ሚያዚያ 22/2012 ባሰፈረው ጽሑፉ ጠቅሷል። ገንዘቡ የሚቀርበው ኢትዮጵያ ያቀደችው የምጣኔ ሀብታዊ ለውጥ አጀንዳን ለመደገፍ ነውም ሲል ኤምባሲው አክሏል።

ቅጽ 2 ቁጥር 78 ሚያዝያ 24 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here