በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች ከመጭው ዓርብ ጀምሮ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአስገዳጅነት መጠቀም እንዳባቸው የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ከመጭው ዓርብ ጀምሮ የሚኒባስ ተጠቃሚዎች የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎችን በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለስልጣን ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተሪ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚህም መሰረት ተሳፋሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት ለመጠቀም ሲንቀሳቀሱ ጭምብሎችን መጠቀም ይኖርባቸዋል ተሳፋሪዎችም ያለ አፍ መሸፈኛ ጭምብል ታክሲ መጠቀም እንደማይችሉ ባለስልጣኑ ማሳሰቢያ ሰጥቷል ፡፡
ከዚህም ጋር በተያያዘ የፐብሊክ ሰርቪስ ድርጅት ከዛሬ ጀምሮ ተሳፋሪዎች የአፍ መሸፈኛ ጭምብል በአስገዳጅነት እንዲጠቀሙ ማስታወቁ የሚታወስ ነው።




