በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ ለ1764 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 11 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትር አስተወቀ።
እንደ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለፃ ቫይረሱ ከተገኘባቸው 11 ሰዎች ውስጥ 10 ወንዶች እና አንዷ ሴትሲሆኑ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ናቸው።
እድሜያቸው ከ18 እስከ 38 አመት መሆኑንም ነው ሚኒስትሯ ያስታወቁት።
ግለሰቦቹ እድሜያቸው ከ18 እስከ 38 አመት ሲሆኑ አምስቱ ከአዲስ አበባ፣ ሁለቱ ከትግራይ ክልል ለይቶ ማቆያ፣ ሶስት ሰዎች ከአፋር ክልል ለይቶ ማቆያ እንዲሁም አንድ ግለሰብ ከኦሮሚያ ክልል አዳማ ለይቶ ማቆያ መሆናቸው ታውቋል።
በተጨማሪም አምስቱ የውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆኑ ስድስቱ ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው ናቸው ተብሏል።
በአጠቃላይ እስካሁን ከቫይረሱ ጋር በተያያዘ ለ36 ሺህ 624 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ በአሁኑ ሰአት 138 ሰዎች በህክምና ላይ ሲሆኑ፤ ስድስት ተጨማሪ ሰዎች ደግሞ ከቫይረሱ ማገገማቸው ተገልጿል፡፡





