የኮሮና ቫይረስ ምልክቶችን የሚመረምር እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የሚያጣራ አዲስ መተግበሪያ ይፋ ሊሆን ነው

0
832

ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች የኖቭል ኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው የሚመረምር እና ብሉቱዝን በመጠቀም ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የሚያጣራ መተግበሪያ በያዝነው የፈረንጆቹ ወር ይፋ ለማድረግ ማቀዱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡

ይህ መተግበሪያ ሰዎች ስለሚታይባቸው ምልክት በመጠየቅ የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው ወይም እንደሌለባቸው መመሪያ ይሰጣል ሲሉ የአለም ጤና ድርጅት የመረጃ ክፍል ሀላፊ በርናንዶ ማሪያኖ ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ለመመርመር የሚረዱ ሌሎች መረጃዎች በተጠቃሚው ሀገር መሠረት እንዲካተቱ ይደረጋሉ ተብሏል ፡፡

መተግበሪያውም በዓለም አቀፍ መተግበሪያዎች ስቶር ላይ የሚለቀቅ ሲሆን ፣ ማንኛውም አገር የመተግበሪያውን ቴክኖሎጂ ሊወስድ እና ማሻሻያዎችን በማከል የራሱን በመተግበሪያ ስቶር ላይ መልቀቅ እንደሚችል ማሪያኖ ተናግረዋል፡፡

መተግበሪያው በርካታ አገራት ንክኪ ያላቸውን ሰዎችን ለመፈለግ የሚያደርጉትን ጥረት ሊያፋጥን እንደሚችልም ተገምቷል፡፡

የዓለም የጤና ድርጅት ቫይረሱ እየጨመረ የሚገኝባቸውን ደቡብ አሜሪካ እና በአፍሪካ ያሉትን ጨምሮ በሌሎች ሀገራት ውስጥ ፍላጎት እንደሚጨምር ይጠበቃል፡፡

ቴክኖሎጂው ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ማንነታቸው ሳይገለጽ ለቫይረሱ ያላቸውን ተጋላጭነት ከመረዳት ባሻገር የቅርብ ጊዜ ግንኙነቶች እንዲየጣሩ ይረዳል ተብሏል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ አፕል እና ጉግል ማንኛውንም መረጃ ለሌላ ዓላማዎች እንደማይጠቀምና ወረርሽኙ ሲያበቃም እንደሚቆም ተናግረዋል፡፡

ህንድ ፣ አውስትራሊያ እና እንግሊዝ ቀድሞውኑ የራሳቸውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ኦፊሺያላዊ የቫይረስ መተግበሪያዎችን ማውጣታቸውን ሮይተርስን ዋቢ አድርጎ ኢ ቢ ሲ ዘግቦታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here