የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የ9 ወራት የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርትን ዛሬ ገምግሟል ፡፡

0
851

በባለስልጣን መስራቤቱ የሶስተኛው የሩብ አመት የእቅድ አፈጻጻም ሪፖርት የቪዲዮ ኮንፈረንሱ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ዳይሬክተሮች አማካሪዎችና የቡድን መሪዎች ታድመዋል።

በሪፖርቱም ባሳለፍነው 9 ወራት በዋና መንገዶች ማጠናከርና ደረጃ ማሻሻል 77 ኪ .ሜ መንገድ እና በአገናኝ መንገዶች ደረጃ ማሻሻልና ግንባታ እንዲሁም በመንገዶች ከባድ ጥገና 1 ሺህ 183 ኪ .ሜ ተሰርቷል ተብሏል፡፡

በተመሳሳይም በመንገዶች ወቅታዊ ጥገና 377 ኪ. ሜ እና በመደበኛ ጥገና 6 ሺህ 519 ኪ .ሜ ማከናወን የቻለ ሲሆን በድምሩ 8 ሺህ 156 ኪ .ሜ በላይ የፊዚካል የመንገድ ግንባታ ስራዎችን ማከናወኑ ተገልጿል፡፡ በዚህም ባሳለፍነው ዘጠኝ ወራት አጠቃላይ አፈጻጻሙ በዋና ዋና የመንገድ ግንባታ ስራዎች 70 በመቶ ሆኖ ተመዝግቧል።

በውይይቱም ለመንገድ ፕሮጀክቶች መዘግየት መንስኤዎች ከወሰን ማስከበር እና ከካሳ ክፍያ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች እንዲሁም የተቋራጮች አቅም ማነስ ዋነኛዎቹ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር ሃብታሙ ተገኘ በዘርፉ ያሉ መሰል ችግሮችን ለመቅረፍ በተለይም ከባለድርሻ አካላት ጋር አሁንም በቅርበት በመስራት የዘርፉን አፈጻጻም ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ትኩረት እንደሚደረግ ተናግረዋል ።

በበጀት አመቱ ዕቅድ ከተያዘላቸው የመንገድ ግንባታ ጨረታዎች መካከል ባለፉት ዘጠኝ ወራት 15 የመንገድ ፕሮጀክቶች የግንባታ ውል ስምምነት የተፈረመ ሲሆን በተጨማሪም የ42 ፕሮጀክቶችን የግዥ ሂደት ለማጠናቀቅ እና 26 ፕሮጀክቶችን ወደ ግዥ ሂደት ለማስገባት ታቅዶ እየተሰራ ነው ተብሏል፡፡

ባለስልጣን መ/ቤቱ ፕሮጀክቶችን በቅርበት ከመከታተልና ከመደገፍ ባለፈ የተቋሙን የአቅም ግንባታ የሚመለከቱ በርካታ ሥራዎች በበጀት አመቱ እያከናወነ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ከእነዚህም ሥራዎች ውስጥ የሞደርናይዜሽን እና ትራንስፎርሜሽን ጥናቱ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደ ተግባር መሸጋገሩ ተመላክቷል ።
ከምህንድስና ግዥ፣ ከዲዛይን፣ ከኮንትራት ማኔጅመንት፣ ከመንገድ ሀብት ማኔጅመንት እና ተያያዥ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ እየተሰሩ የሚገኙ የሞደርናይዜሽን ጥናቶች ወደ ስራ ተቀይረው ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስገኙ እንደሆነ መገምገሙንም ከመንገዶች ባለስልጣን መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመክታል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here