በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቴድሮስ አደባባይ ቅርንጫፍ የጥበቃ ሰራተኛ የነበረች ሴት ከወንድ ባልደረባዋ በተተኮሰባት ጥይት ህይወቷ ማለፉ ተገለፀ፡፡
አዲስ ማለዳ አደጋው ተከሰተ በተባለበት ስፍራ ተገኝታ ለማረጋገጥ እንደቻለችው የጠበቃ ሰራተኛዋ ህይወት ሊያልፍ የቻለው ከባልደረባዋ በተተኮሰ ጥይት ጀርባዋ ላይ በመመታቷ ሲሆን ህይወቷን ለማትረፍ በአፋጣኝ ወደ ህክምና መስጫ ተቋም ብትወሰድም ህይወቷን ለማትረፍ ሳይቻል ቀርቷል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የአደጋውን መንስኤ እያጣራ መሆኑ ታውቋል፡፡



