ይህም እስካሁን ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 261 አድርሶታል።
በዛሬው እለት ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸውም ከ19-47 ዓመት የሆኑና ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው።
ከነዚህም 11 ሰዎች ውስጥ 8ቱ ከአፋር ክልል ሰመራ ለይቶ ማቆያ የነበሩ፣ 1 ከትግራይ ክልል መቐለ ለይቶ ማቆያ፣ 1 ከሶማሌ ክልል ጂግጅጋ ለይቶ ማቆያ እና 1 ሰው ከአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አጣዬ ከተማ ለይቶ ማቆያ የነበሩ መሆናቸውም ታውቋል።
በአጠቃላይ ቫይረሱ ተገኝቶባቸው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ ሰዎች 148 መሆናቸውንም ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ትላንት ከአዲስ አበባ አንድ ሰው ከበሽታ ያገገመ ሲሆን በአጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 106 ደርሷል።
እስካሁን አጠቃላይ 39 ሺህ 048 የላቦራቶሪ ምርመራ መከናወኑንም ከዛሬው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል።





