የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ የ2012 የ9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ውይይት አካሄደ

0
538

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ (ኢመደኤ) የ2012 የ 9 ወር የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተሮች በተገኙበት ለተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡

በውይይቱ ወቅት ኤጀንሲው በሳይበር ደህንነት ዘርፍ የተለያዩ ጥናትና ምርምሮችን ማድረጉ፣ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡና በሚወጡ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ ቁጥጥር ማከናወኑ፣ በሀገሪቱ ላይ ሊቃጡ የሚችሉ የሳይበር ጥቃቶችን በመከላከል እንዲሁም የተቋማትን አሰራር በማዘመን በኩል ፋይዳቸው ከፍተኛ የሆኑ ሥራዎችን ባለፉት 9 ወራት ማከናወን መቻሉን በሪፓርቱ ላይ ተገልጿል፡፡

በተያያዘም ኤጀንሲው ቀጠናዊ እና አለም አቀፋዊ ተጽእኖ ፈጣሪ እንዲሆን ከማድረግ አንጻር በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው የተዘጋጀ ቴክኖሎጂ ዴቨሎፕመንት እና ፕሮዳክት ኮሜርሻይሌዜሽን ̋ በሚል አዲስ ሮድ ማፕ የቀረበ ሲሆን በቀጣይም በዚሁ ሮድ ማፕ ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማድረግ በተጨማሪ ሀሳቦች እንዲዳብር ይደረጋል ተብሏል፡፡

ከዚህም ከቀረበው 9 ወር የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ባሻገር ለኤጀንሲው ም/ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ዶክተር አንተነህ ተስፋዬ ከኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ትውውቅ ማድረጋቻን ከኤጀንሲው የፌስ ቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here