ባለፈው ዓመት የተተከሉ ችግኞች 84 በመቶ መፅደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ

0
713

በባለፈው ዓመት የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተተከሉት ችግኞች 84 በመቶ የሚሆኑት መፅደቃቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በፌስ ቡክ ገፅ ባሰፈሩት ፅሁፍ እንደገለፁት በአረንጓዴ ዐሻራ የችግን ተከላ ወቅት በሀገር አቀፍ ደረጃ የተተከሉት ችግኞች እንዲያድጉ በመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ የመንከባከብ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ገልፀዋል።

ከተተከሉትም ችግኞች ውስጥ በአማካይ 84 በመቶ የሚሆኑት መፅደቃቸውም ለመጭው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በምንዘጋጅበት በዚህ ወቅት፣ ጥረታችን ፍሬ ማፍራቱን መገንዘባችን ተስፋ ሰጭ ነው ሲሉ አስታውቀዋል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here