የኮቪድ-19 በሽታ ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ ደቦ የተሰኘ የሰዎች ንክኪ መለያ የአንድሮይድ ስልክ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ

0
794

ይህ ዶቦ የተሰኘው የንክኪ መለያ የአንድሮይድ መተግበሪያ የስልክን የብሉቱዝ ሞገድ በማብራት የራሱን የብሉቱዝ ፕሮቶኮል ተጠቅሞ ከሁለት ሜትር በታች ቅርበት ያላቸውን ሰዎች በስልካቸው ላይ ያለውን መለያ ቁጥር እንዲለዋወጡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህም ቁጥር በሁለቱም ስልኮች ላይ በሚስጥር የሚቀመጥ ሲሆን ንክኪን የሚለየው ቡድን በበሽታ የተያዘውን ሰው ስልክ በመጠቀም ከደቦ ላይ ድብቅ ቁጥሮቹን በመለየት ከተያዘው ሰው ጋር ቅርበት ወይም ንክኪ ሊኖራቸው የሚችሉ ሰዎችን ወዲያውኑ ያገኝዋችዋል ተገቢውንም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ እንዲሁም ተገቢውን ክትትል ያደርጋል ተብሏል።

በተጨማሪም መተግበሪያው የአንድ ግለሰብን የቀን ውሎውን መመዝገብ የሚያስችል ነው፡፡

ይህምመተግበሪያው የአንድሮይድ ስልክ የማይጠቀሙ በአቅራቢያዎ ይበልጥ ተጋላጭ እና ንክኪ ያላቸው ሰዎች በየእለቱ በዲያሪ ላይ ስልካቸውን ስማቸውን እና ጾታቸውን በመመዝገብ በቀላሉ እንዲለዩ ማድረግ እንደሚችልም ተገልጿል፡፡

ስለሆነም ማህበረሱ ደቦ መተግበሪያን መተግበሪያን https://debo.ephi.gov.et ከሚለው ድረ ገጽ በመውሰድ በስልኩ ላይ በመጫን በስልኩ ላይ በመጫን እንዲሁም የሚገኙ ወዳዶቾን እንዲጭኑት በመርዳት የኮቪድ -19 ስርጭትን በጋራ እንዲከላከል ኢንስቲዩቱ ጥሪውን አቅርቧል።

ተጠቃሚዎች መተግበሪያውን ካወረዱ በሗላ ለመዝገባ ቅጹን ሞልተው እስኪጨርሱ ድረስ ኢንተርኔት ክፍት ማድረግ እንደሚገባቸውም ተገልጿል።

በተጨማሪም የአንድሮይድ 9 እና 10 ተጠቃሚዎች የብሉቱዙን መለያ ከsetting ውስጥ ወስደው ሳይሳሳቱ መሙላት እንደሚችሉም ለማወቅ ተችሏል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here