አትላንታ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የ10 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸው ተገለፀ

0
830

አትላንታ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት ኮቪድ-19ን ለመከላከል የ10 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጋቸውን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ ገለፁ።

አምባሳደሩ በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት መልእክት እንዳሉት “ለወገን ደራሽ ወገን ነው!” በሚል መሪ ቃል ከኮሚኒቲው አባላት ጋር ውይይት ማድረጋቸውን እና በዚሁ ወቅት 10 ሺህ ዶላር መሰብሰብ መቻሉን አስታውቀው ድጋፉን ላደረጉ የኮሚኒቲው አባላትም ምስጋቸውን አቅርበዋል፡፡

በቀጣይም ይህንን የመሰሉ ውይይቶች እና ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉም አምባሳደሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here