የሶስቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገራት ቴክኒካዊ ምክክር ዛሬ ይጀመራል

0
934

ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን የውሃ፣ መስኖና ኢንጂነር ሚኒስቴሮች ቴክኒካዊ ምክክር እና ድርድር ዛሬ እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ከሶስቱ የአባይ ተፋሰስ ሀገሮች የውሃ፣ መስኖና ኢንጂነር ሚኒስቴሮች በቪዲዮ ኮንፈረንስ እንደሚገናኙ የሱዳን የመስኖ ልማት ሚኒስትር አስታወቋል፡፡

ይህን ውይይትም በተሳካ ሁኔታ ለማስቀጠል የሱዳን የመስኖ ልማት ሚኒስትር ከፍተኛ ሚና የተጫወተ ሲሆን “ከአሜሪካ ፣ ከአውሮፓ ህብረት እና ከደቡብ አፍሪካ ሶስት ታዛቢዎች በምክክሩ ላይ እንደሚሳተፉም ለማወቅ ተችሏል ፡፡

ከዚህ ቀደም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሀምዶክ ጋር በግድቡ አሞላል እና ተያያዥ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ዙሪያ በመወያየት ስምምነት ላይ መድረሳቸው፤ እንዲሁም ይህም ውይይት እና ምክክር በግብፅ በኩል ይሁንታን ማግኘቱም የሚታወስ ነው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኢትዮጵያ በያዘችው እቅድ መሰረት የታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሀ ሙሌት በያዝነው የክረምት ወራት ውስጥ እንደምትጀመር ይፋ ማድረጓ የሚታወቅ ነው፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here