ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ 190 ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ፤ የተጨማሪ 5 ሰዎች ህይወትም አልፏል

0
825

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰአታት ውስጥ በተደረገ 4,599 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 190 ሰዎች ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን እንዲሁም የ5 ተጨማሪ ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስቴሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ እንደገለፁት ቫይረሱ የተገኘባቸው 135 ወንድ እና 55 ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ ከ1 እስከ 89 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውም ታውቋል፡፡

ይህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙትን ሰዎች ቁጥር 2,336 ያደረሰው ሲሆን በቫይረሱ ሳቢያ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥርም 32 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በትናንትናው እለት ሪፖርት በተደረገው የዕለታዊ መግለጫ ላይ ቫይረሱ በምርመራ እንደተገኘባቸው ከተገለፁት 136 ሰዎች ውስጥ 10 ሰዎች ከዚህ በፊት ሪፖርት ተደርገው በህክምና ማዕከል ውስጥ ያሉ እና ክትትል እየተደረገላቸው የሚገኙ  በመሆናቸው 136 የተባለው እለታዊ ሪፖርት 126 በሚል እንዲስተካከል ሲል የጤና ሚኒስቴር በመግለጫው ላይ አስታውቋል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here