የቀጣዩ ዓመት በጀት ድልድል ላይ የሲዳማ ክልል አለመካተቱ ተቃውሞ አስነሳ

0
892

በኢትዮጵያ ለ2013 በጀት ዓመት የጸደቀውን በጀት ተከትሎ ለክልሎች የተከፋፈለው ዓመታዊ በጀት ሲዳማ ክልልን አለማካተቱ ከምክር ቤት አባላት ዘንድ ተቃውሞ ተሰምቶበታል።

አስራ አንደኛ ክልል በመሆን በቅርቡ በክልል ደረጃ የተዋቀረው ሲዳማ ክልል በአዲሱ የክልሎች በጀት ድልድል ወቅት ከፌደራል መንግስት ታሳቢ ተደርጎ አለመካተቱ እና በቅርቡ ሕዝባዊ ውሳኔ ተካሒዶበት በክልልነት ከተደራጀ በበጀት ድልድሉ አለመካተቱ የሕዝብን ድምጽ መናቅ ተደርጎ ይቆጠራል የሚል ተቃውሞ ተሰምቶበታል። በተመሳሳይም የምክር ቤት አባል የሆኑት ጴጥሮስ ወልደሰንበት የሲዳማ ጉዳይ ቀድሞ ያለቀ ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን ለቀጣዩ ዓመት የበጀት ድልድል ወቅት ለምን ሳይካተት ቀረ የሚል ጥያቄም ለገንዘብ  ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ አቅርበዋል።

ዛሬ ሰኔ 4/2012 የቀጣዩን ዓመት 2013 በጀትን በተመለከተ ረቂቅ የቀረበ ሲሆን በወቅቱም የገንዘብ ሚኒስቴር አሕመድ ሽዴ ከምክር ቤቱ ለቀረበው ጥያቄ ምላሽ ሰጥተዋል። ሚንስትሩ በምላሻቸውም በጀቱ የተሰራው ከፌደሬሽን ምክር ቤት ተሰርቶ በሚመጣ ቀመር ሲሆን ከፌደሬሽን ምክር ቤት ሴዳማ ክልልን ያካተተ ቀመር ባለመሰራቱ በረቂቁ ላይ አለመካተቱን እና የፌደሬሽን ምክር ቤት ሲዳማ ክልልን ያካተተ ቀመር በላከ ጊዜ ድልድሉን መስራት እንደሚቻል አስታውቀዋል።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበው የቀጣዩ ዓመት በጀት ረቂቅ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here