የኮሮና ምርመራን በተወሰነ ስፍራ ብቻ መከናወኑ ለቁጥሮች መዋዠቅ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ

0
551

ከውጭ አገራት ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በድንበር እና በሌሎች የለይቶ ማቆያ ስፍራዎች እዲቆዩ የሚደረጉ እና ከእነርሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች በዋናነት ትኩረት አድርጎ ምርመራ ማካሔዱ ለምርመራ ቁጥሩ መዋዠቅ ምክንያት መሆኑ ተገለጸ።

የጤና ሚንስቴር የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዩርዳኖስ አለባቸው ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት ኢትዮጲያ አሁን ባለው ደረጃ የመመርመር አቅሟ አስከ 6 ሺህ ነው መባሉን ተከትሎ በየ ቀኑ የሚወጡት የተመረመሩ ሰዎች ቁጥር የሚቀንሰው እና የሚጨምረውን ምክንያት አሁን እየተመረመረ ያለው በድምበር አካባቢ እየገቡ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ያሉ ሰዎችን ነው ብለዋል። የነሱ ውጤት ከታወቀ ደግሞ ከነሱ ጋር ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የመመርምር ስራ ይሰራል በዛ መሃል ቁጥር ማነስ እና ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየት ይመጣል ብለዋል።

ይሁን እና አሁን ከዛ ውጪ አብዛኘውን እየተመረመረ ያለው 8535 ላይ ወይም 952 እየደወሉ የሚመጡ ሰዎች እና ድንገት ምልክቱን ሲያዩ በጥርጣሬ የሚመጡ እንደሆኑ ዮርዳኖስ ለአዲስ ማለዳ ጨምረው ተናግረዋል።

እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለፃ ከሆነ በኢትዮጲያ ውስጥ አሁን ያለው የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ከእለት ወደ እለት አቅጣጫውን እየቀየረ የስርጭት መጠኑ ደግሞ እየጨመረ በመምጣቱ ምክንያት ህብረተሰቡ ውስጥ መሰራጨቱንም ለማወቅ ተችሏል።

ነገር ግን ይላሉ ዮርዳኖስ ንክኪ የላቸውም ተብሎ መረጃው ይሰራጨች እንጂ ‹‹ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት የሌላቸው እና በምን መንገድ እንደተያዙ ግልፅ የሆነ መረጃ ስሌላቸው ግለሰቦች እንደዛ ተብሎ እንደሚቀመጥ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጲያ ውስጥ አስከ መጋቢት አራት ድረስ የመጀመርያው ተጠቂ ይፋ ሆኖ ከሱ ጋር ንክኪ ያለቸውብቻ ነበሩ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው የታወቀው።

ዮርዳኖስ እንደሚሉት ከሆነ አሁን (community transmission ) በመሆን ህብረተሰቡ ውስጥ ዘልቆ ስለገባ ግንኙነት የላቸውም ተብሎ የሚወጣው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች እየጨመሩ ነው ።

ዚህም የመጀመርያው ተጠቂ ይፋ ከተደረገ በኃላ እና ግንኙነት ሌላቸው ተጠቂዎች መገኘት ከጀመሩ በኋላ የመጀመር ደረጃውን አልፈዋል ብለዋል።
የአለም ጤና ድርጅት ይፋ ባደረገው ደረጃዎች መሰረት አሁን ኢትዮጲያ ሦስት የስርጭት ደረጃዎቸን አልፋ አራተኛው ደረጃ ላይ ናት ፤ የመጀመርያው 1low (clear) confirmed case) አስከ መጋቢት አራት ይፋ የተደረገው የመጀመርያው ተጠቂ ነው።

ኹለተኛው ስርጭት ሂደት (firset confirmed case ) ከዛ በኋላ የመጡት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ንክኪ ካላቸው ጋር ሲወጡ የነበሩት አዚ ደረጃ ላይ የነበሩ ሲሆን ሶስተኛው ደግሞ (cluster confirmed case) (group case ) ከውጭ ሃገር የጉዞ ታሪክ ካለው ጋር ንክኪ ካላቸው ሰዎች ጋር የተገኙ ናቸው ።

አራተኛው እና የመጨረሻው (community transmission) ይሄ ደግሞ ማኅበረሰብ ውስጥ የገባ ስርጭት እና ማን ከማን ጋር ግንኙነት እንዳለው በግልጽ ለማወቅ የሚከብድበት ወቅት ሲሆን ነው። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ዮርዳኖስ ለአዲስ ማለዳ እንደተናገሩት ከሆነ አሁን ኢትዮጲያ ያለችበት ደረጃ ይሄ መሆኑን ተናግረዋል።

ቅጽ 2 ቁጥር 84 ሠኔ 6 2012

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here