የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ለመጀመሪያ ግዜ የባቡር ካፒቴኖች አስመርቋል።
የኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ላለፉት 6 ወራት በሃገረ ቻይና ስልጠናቸውን ሲከታተሉ የቆዩ 34 ኢትዮጲያውያን የአዲስ አበባ- ጅቡቲ የኤሌክትሪክ የባቡር ካፒቴኖችን ለመጀመሪያ ግዜ ማስመረቁ ታውቋል፡፡
የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ባስተላለፉት የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ተመራቂዎች ወደ ስራ ሲገቡ ህዘባቸውን በታማኝነት እነደሚያገለግሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በዘርፉ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሸግግርን እውን ለማድረግ ሚኒሰቴር መስራቤቱ እየሠራ መሆኑን መግለፃቸውን ከትራንስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።



