ዲግዛሜታሶን የተሰኘ ህይወት አድን የኮሮና መድሃኒት ተገኘ

0
631

በጽኑ የኮሮና ሕመም ላይ ያሉ ሰዎችን የሚፈውስ ዲግዛሜታሶን የተባለ አዲስ መድሃኒት መገኘቱን የብሪታኒያ ተመራማሪዎች አስታወቁ፡፡

አርትራይተስ ፣ ከባድ አለርጂዎች እና የአስም በሽታን ለማከም ያገለገለው ይህ የፀረ-ኢንፌርሽን መድኃኒት ፣ የሰዎችን ሕይወት ለመታደግ የታየው የመጀመሪያው መድሃኒት ሲሆን ባለሙያዎቹ ውጤቱን እንደ “ታላቅ ግኝት” አይተውታል፡፡

ሳይንቲስቶቹ በህክምና ላይ ያሉና በቬንትሌተር የሚተነፍሱት ታማሚዎችን የመሞት እድል በሶስት እጥፍ እንደሚቀንስ የገለጹ ሲሆን በኦክስጅን ውስጥ ያሉትን የመሞት ዕድላቸውን በአምስት እጥፍ እንደሚቀንስ አስታውቀዋል፡፡

ይህ የተገኘ የተባለው መድሃኒት የኮሮና ቫይረስን ለማከም በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተደረጉ ትልልቅ ሙከራዎች አንዱ መሆኑንም ነው የቢቢሲ ዘገባ የሚያመለክተው፡፡

ተመራማሪዎቹ የኮሮና ቫይረስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ይህ መድሃኒት ጥቅም ላይ ውሎ ቢሆን ኖሮ የአምስት ሺ ሰዎችን ሕይወት ማትረፍ ይቻል እንደነበርም ተናግረዋል፡፡

ኮሮናቫይረስ ከተገኘባቸው 20 ሰዎች 19ኙ መድሃኒቱን በመውሰድ ብቻ ሆስፒታል መሄድ ሳይጠበቅባቸው በቤታቸው ሆነው መዳን ይችላሉ ተብሏል።

መድሃኒቱ ዋጋው በጣም አነስተኛና ለድሃ ሀገራትም ጭምር በቀላሉ ሊገዙት የሚችሉት መሆኑ ተገልጿል፡፡
ከ20 ታማሚዎች 19 የሚሆኑት መድሃቱን ከወሰዱ ሆስፒታል ሳይሄዱ መዳን እንደሚችሉም ተገልጿል ሲል ከ ቢቢሲ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here