የደንበኞች የኦንላይ አገልግሎትን ለመጀመር ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ

0
1006

የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከልና የደንበኞችን ጊዜና ወጪ ለመቆጠብ የጉምሩክ አገልግሎት በኦንላይ ለመስጠት የጉምሩክ ኮሚሽን ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይህ የተገለፀው የጉምሩክ አገልግሎትን ለማዘመን ከኮሚሽኑ ጋር እየሰራ የሚገኘው እና ሶፍትዌር በማልማት ስራ የተሰማራ “ዌብፎንቴይን” የተሰኘ ድርጅት ለኮሮና መካከል እንዲያግዝ ያደረገው ድጋፍ ርክክብ በተካሄደበት ወቅት ነው፡፡

ዌብፎንቴይን 550ሺህ ብር የሚገመት ለኮሮና መከላከል የሚውል የቁሳቁስ ድጋፍ ለጉምሩክ ኮሚሽን አስርክቧል፡፡ የጉምሩክ ኮሚሽንን በመወከል ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና የዌብፎይቴን የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ኤልያስ ክ/ማርያም ርክክብ ያደረጉ ሲሆን ቁሳቁሶቹ 5 የኦክስጂን ማምረቻ (ኦክስጂን ኮንሰንትሬሽን) እና 26 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭንብሎች ናቸው፡፡

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ደበሌ ቃበታ በድጋፉ ወቅት፤ ለኮሮና መከላከል የተደረገው ድጋፍ ተጋላጭ ለሆኑ ሰራተኞችና ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት በመስጠት ለታለመው አገልግሎት እንዲውል ይደረጋል ያሉ ሲሆን ለተደረገውም ድጋፍ በገቢዎች ሚኒሰቴርና ጉምሩክ ኮሚሽን መላው አመራርና ሰራተኛ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የዌብፎንቴይን ተወካይ አቶ ኤልያስ ክ/ማርያም በበኩላቸው ድርጅቱ በአፍሪካ ለአስር አገራት ለኮሮና መከላከል ድጋፍ ማድረጉን ጠቁመው ከዚህ ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ እንደሆነች ገልፀዋል፡፡ “ኮሚሽኑ የተደረገው ድጋፍ ለተገቢው አገልግሎት እንደሚያውለው ዕምነት አለን” ማለታቸውን ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here