የሸማ ጥበብ ስራን በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን የሚያስችል የማዕከል ግንባታ መጀመሩ ተገለፀ

0
557

የሸማ ጥበብ ስራን በዘመናዊ መንገድ ለማከናወን የሚያስችል ዘመናዊ የማዕከል ግንባታ መጀመሩን የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ዑማ አስታወቁ፡፡

ምክትል ከንቲባው ዛሬ በፊስቡክ ገፃቸው እንዳሰፈሩት “የአገራችን ጠቢባን እጅ ስራ ግሩም ድንቅ ሆኖ ፈትል ሸምኖ ሲያሞቀን ሲያደምቀን ኖሯል፡፡

ጠቢባኑን ግን በሚመቻቸው መንገድ እንዲሰሩ፣ ስራቸው ተስፋፍቶ ሸማቸው አገር ከማልበስ ተሻግሮ ለአገር ኢኮኖሚ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አልተደረገም” ያሉ ሲሆን።

“በከተማችን ብዙ የሸማ ጥበብ ስራ በሚሰራበት ሽሮ ሜዳ ማዕከል ሆኖ የሚያገለግል ግንባታ ጀምረናል።

ከጥበቡ “ሸማ”ን ከሰፈሩ “ሜዳ”ን ወስደን የወደፊቱን የኢትዮጲያ ጥበብ ማበልፀጊያ ማዕከል “ሸማ ሜዳ”ን በፍጥነት አጠናቀን ለአገልግሎት እናበቃለን” ሲሉ ገልፀዋል።

 

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here