ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሱዳኑ ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ጋር የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ይገኛሉ

0
946

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌፍተናንት ጀነራል መሐመድ ሐምዳን ዳግሎ የአዳማ የኢንዱስትሪ ፓርክን እየጎበኙ ነው።

በጉብኝቱ ላይም የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት እየተሳተፉበት ይገኛሉ።

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ምክትል ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ሃምዳን ደጋሎ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር በትናንትናው እለት አዲስ አበባ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

መልስ አስቀምጡ

Please enter your comment!
Please enter your name here